የሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን ለ2017 በጀት ዓመት በክልሉ ውስጥ የመንገድ ግንባታ እና ጥገና ሥራ ለማሠራት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የኮንስትራክሽን ማሸነሪዎች መስፈርቱን ከሚያሟሉ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አውዳደሮ መከራየት ይፈልጋል፡፡
የሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን (Sidama Roads Authority)
ድጋሚ የወጣ የማሽን ኪራይ አገልግሎት ግዥ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር ሲ/መ/ባ/0031/2017
የሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን ለ2017 በጀት ዓመት በክልሉ ውስጥ የመንገድ ግንባታ እና ጥገና ሥራ ለማሠራት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የኮንስትራክሽን ማሸነሪዎች መስፈርቱን ከሚያሟሉ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አውዳደሮ መከራየት ይፈልጋል፡፡
|
ተ.ቁ |
የማሽን ዓይነት |
ብዛት |
|
1 |
ግሬደር |
10 |
|
2 |
ሮለር |
10 |
በዚሁ መሠረት :-
- ተጫራቾች አግባብነት ያለውን ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ታክስ ክሊራንስ እንዲሁም የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ለመመዝገባቸውን የሚያሳይ ተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 (ሦስት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 (አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት ከባለሥልጣኑ መ/ቤት ግዥ የፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቀርበው መግዛት ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም ከታወቀ ባንክ የቀረበ የጨረታ ማስከበሪያ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ዋስትና (Unconclitional Bid) ከጠቅላላው ዋጋ 0.5% ሆኖ ከ 500,000 ብር በላይ የሚበልጥ ከሆነ ብር 500,000 ብቻ CPO ወይም ባንክ ጋራንት በማሰራት ለብቻው በማሸግ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ከባንከ የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) ለ180 ቀን ፀንቶ የሚቆይ መሆን ይኖርበታል፡፡
- የሚቀርቡ ማሽነሪዎች በሙሉ የፈረስ ጉልበታቸው፣ የስሪት ዘመናቸው እና ሌሎች መጫረቻ ሰነዱ ላይ የተገለጹ መስፈርቶችን የሚያሟሉ መሆን አለባቸው፡፡
- የሚቀርቡ ማሽነሪዎች ወደ ሥራ በሚሰማሩበት ጊዜ እና ከአንዱ ፕሮጀከት ወደ ሌላ ፕሮጀከት ማሽነሮችን ማንቀሳቀስ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ አሸናፊው ድርጅት በራሳቸው ወጪ አጓጉዘው ወጪው በባለስልጣኑ መ/ቤት የሚሸፈን ይሆናል፡፡
- የሚቀርቡ ማሽነሪዎች የኢንጂን ሠዓታቸው እና የነዳጅ ኦዲዮሜትር በትከክል የሚሰራ መሆን አለበት፡፡
- ከዚህ በፊት ከሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን ጋር ውለታ ገብቶ በአፈጻጸም ችግር ምከንያት ማስጠንቀቂያ ተሰቶት ማሽነሪዎችን ወደ ስራ ያላስገባና ውላቸው የተቋረጠ የማሽነሪ አከራይ ድርጅት የጨረታ ሰነዱን መግዛትም ሆነ መወዳደር አይችልም፡፡
- የጨረታ ሰነዱ በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ተሞልቶ ጨረታ ማስከበሪያ /Bid Security/ ፋይናንሻል አንድ ዋና (ኦርጅናል) እና ሁለት ኮፒዎችን እንዲሁም ቴክኒካል አንድ ዋና (ኦርጅናል) እና ሁለት ኮፒ ሰነዶችን በተለያየ ፖስታ በሰም በማሸግ ለየብቻቸው ታሽጎ በአንድ እናት ፖስታ ውስጥ ተከተውና በሁሉም ዶክመንት ላይ ስምና አድራሻ በመጻፍ ህጋዊ የሆነ ማህተም በመምታት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛ ከጠዋቱ 4፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት በሲዳማ መንገዶች ባለሥልጣን በግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ክፍል ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ማስከበሪያው ከቴክኒካል ሠነድ ጋር አብሮ መታሸግ አለበት፡፡ ከላይ የተጠቀሰው ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የእረፍት ወይም የህዝብ በዓል ቀን ሆኖ ከዋለ በቀጣይ በሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ የሚከፈት ይሆናል፡፡
- በጨረታ ሰነድ ላይ የተጠቀሱትን የጨረታ መመሪያ እና ህጎች አለማክበር በመጫረቻ ሰነዶቻቸው በሁሉም ገጽ ላይ ማህተምና ፊርማ ያለማድረግ እና ያልተፈረመበት ስርዝ ድልዝ ያለበት የመጫረቻ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ የጨረታ መክፈቻ ተብሎ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ በባለስልጣኑ መ/ቤት አዳራሽ ይከፈታል።
ማሳሰቢያ፡- ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ስልክ ቁጥር 0462-128 446
የሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን
ሐዋሳ
