Tender Detail

Tender Details

  • Company የአዳማ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
  • Address አዳማ በከልቻ ትራንስፖርት አክሲዮን ማህበር አጠገብ ያለው ቢሮአችን ሦስተኛ (3) ፎቅ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 022-211-58-07
  • Website
  • Deadline08 Dec 2024, 10:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Vehicle

የአዳማ ጉምሩከ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት አስመጪ አቶ ዮናስ ፈለቀ ጥበቡ ላልከፈሉት ቀሪ ቀረጥና ታክስ ዕዳ ማካካሻነት የያዛቸውን HYUNDAI እና TOYOTA COROLLA ተሽከርካሪዎችን በግልፅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

የአዳማ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት


የግልፅ  ጨረታ  ማስታወቂያ  ቁጥር  16 2017

የአዳማ ጉምሩከ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት አስመጪ አቶ ዮናስ ፈለቀ ጥበቡ ላልከፈሉት ቀሪ ቀረጥና ታክስ ዕዳ ማካካሻነት የያዛቸውን HYUNDAI እና TOYOTA COROLLA ተሽከርካሪዎችን በግልፅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም :-

  1. በአዳማ ጉ/ኮ ቅ/ጽ/ቤት ለጨረታ በቀረቡት ተሽከርካሪዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር የታደሠ መታወቂያ አያይዞ በፖስታ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል፡፡
  2. የግልጽ ጨረታ ሰነዱን የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ ሙሉ ቀን በስራ ሰዓት እና ቅዳሜ ጠዋት ከ2፡00-6፡00 ሰዓት በአዳማ ከተማ በከልቻ ትራንስፖርት አማ ግቢ ውስጥ በሚገኘው የቅ/ጽ/ቤቱ የገቢ ሂሳብና ዋስትናዎች አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 11 የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በመክፈል ማግኘት ይችላሉ፡፡
  3. በግልጽ ጨረታ የሚሳተፉ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ለእያንዳንዱ ተሽከርካሪዎች የሰጡትን የጨረታ መነሻ ዋጋ አምስት በመቶ (5%) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተመሰከረለት (CPO) Customs Commission Adama branch office ስም በማሰራት ለግልፅ ጨረታ በተራ ቁጥር 1 ላይ ከተጠቀሱት ሰነዶች ጋር በማያያዝ በፖስታ በማሸግ በጨረታ ሳጥኑ ውስጥ እንድታስገቡ፡፡
  4. በግልጽ ጨረታ ለሽያጭ ለቀረቡት ተሽከርካሪዎች የጨረታ ሳጥኑ በሚገኝበት በአዳማ ከተማ በሬቻ አካባቢ መ/ቤቱ አዲስ በተከራየው ቢሮ ድረስ በመሄድ በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስፈልገውን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተመሰከረለት CPO እና የታደሰ መታወቂያ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ ሳጥኑ ከመዘጋቱ በፊት ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  5. በጨረታ ለመሸጥ የወጡት ተሽከርካሪዎች በአዳማ ከተማ በከልቻ ትራንስፖርት አ.ማ ግቢ መጋዘን ቁጥር 10 ስለሚገኙ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ከዋለ በኋላ ሳጥኑ በስምንተኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ታሽጐ በ4፡15 ሰዓት የሚከፈት ሲሆን፤ ነገር ግን ስምንተኛው ቀን በዓል ወይም እሁድ ቀን የሚውል ከሆነ ጨረታው የሚካሄደው በተመሳሳይ ሰዓት በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል።
  6. የግልጽ ጨረታ ሳጥኑ የሚከፈትበት ቦታ አዳማ ከተማ በሬቻ አካባቢ መ/ቤቱ አዲስ በተከራየው ቢሮ ቅጥር ግቢ ውስጥ ሲሆን ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እና ታዛቢዎች ባሉበት ይከፈታል፡፡
  7. እሸናፊ ተጫራች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት CPO ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቶች ደግሞ የጨረታው ውጤት በተገለፀ በ3 ሶስት የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
  8. አሸናፊ ተጫራቶች ማሸነፋቸው በማስታወቂያ ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ5 (በአምስት) ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ተሽከርካሪዎቹን መረከብ ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ለጨረታ የቀረቡት ተሸከርካሪዎች ሽያጫቸው የሚፈፀመው ባለበት ሁኔታ ስለሆነ ተጫራቾች ሌላ ተመሳሳይ ወይም ተጨማሪ እቃ መጠየቅ አይችሉም፡፡
  10. ከላይ በተ/ቁ 8 ላይ በተገለፁት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት (CPO) ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ተሽከርካሪው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል።
  11. ማንኛውም በግልጽ ጨረታ የሚሳተፍ ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ዋጋ መቀየር ወይም የሌላ ተጫራችን ዋጋ ተንተርሶ ዋጋ አሻሽሎ ማቅረብ አይችልም፡፡
  12. በአርጅናል ሰነድ ያልተሞላ የዋጋ ማቅረቢያ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
  13. ቅ/ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  14. ማንኛውም ተጫራች 100 ብር ሰነድ የገዛበትን ደረሰኝ ከሌሎች ሰነዶች ጋር አያይዞ በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለበት፡፡
  15. ለጨረታ ማስከበሪያ የምታሰሩት CPO ከኢትዮጵያ ንግድ ባንከ ብቻ መሆን እንዳለበት እና የሌላ ባንከ  የማንቀበል መሆኑን እናሳስባለን፡፡

ለተጨማሪ  መረጃ  በስልክ  ቁጥሮች፡- 0221118429 እና 0222118925 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

 

የአዳማ  ጉምሩክ  ኮሚሽን  ቅ/ጽ/ቤት

Save Tender