በደ/ኢ/ከ/መንግስት በኣሪ ዞን የደቡብ ኣሪ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በፑል ለሚተዳደሩ ሴክተር መ/ቤቶች በ2017 በጀት ዓመት የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን በማወዳደር ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በደ/ኢ/ከ/መንግስት በኣሪ ዞን የደቡብ ኣሪ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በደ/ኢ/ከ/መንግስት በኣሪ ዞን የደቡብ ኣሪ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በፑል ለሚተዳደሩ ሴክተር መ/ቤቶች በ2017 በጀት ዓመት የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን በማወዳደር ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚህም መሰረት ፡-
ሎት 1. የጽህፈት መሳሪያ ዕቃዎች፣ ሎት 2 ሌሎች አላቂ ዕቃዎች ሎት 3 ሞተር ሳይክል በግልጽ ጨረታ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በሁሉም መስኮች ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የ2016 ዓ.ም ፍቃድ ያሳደሱና የንግድ ምዝገባ ወረቀት እና የአቅራቢነት ምዝገባ ሰርተፍኬት የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ፤ የታከስ ክሊራንስ ያለው፡፡
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (tin number) ተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሠርተፍኬት VAT ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እንዲሁም የጨረታ ሰነድ በሚያስገቡበት ጊዜ የድርጅት ማህተም ስም አድራሻ ስልክ ቁጥር እና ፊርማ በሰነዱ ላይ በማድረግ ማቅረብ የሚችል፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚያስገቡበት የሎት 1 የጽ/መሳሪያ 7000 /ሰባት ሺህ ብር/ ፣ ሎት 2. ሌሎች አላቂ ዕቃዎች ብር 7000 /ሰባት ሺህ ብር/ ፣ እና ለሎት 3 ሞተር ሳይክል 10,000 /አስር ሺህ ብር/ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የክፍያ ትዕዛዝ በባንከ የተረጋገጠ CPO ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና በፖስታ ታሽጎ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት ውስጥ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 ሶስት መቶ ብር በእያንዳንዱ ሎት በመክፈል ከኣሪ ዞን ከደቡብ ኣሪ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ከግዥ ን/አስ/ር ዳይሬከቶሬት ክፍል ቀርቦ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
- አሸናፊ ድርጅት ለሚያቀርባቸው ዕቃ የውል ማስከበሪያ ቢያንስ 10% በባንክ በተረጋገጠ /CPO/ ማስያዝ የሚችል፡፡
- አሽናፊ ተጫራች ያሸነፈውን ዕቃዎች እስከ በደ/ኢ/ከ/መንግስት በኣሪ ዞን የደቡብ ኣሪ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ድረስ በማምጣት ማስረከብ የሚችል፣
- ተጫራቾች ባሸነፉበት ዕቃ ውል ገብተው ለማቅረብ ፍቃደኛ ባይሆኑ የውሉ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ሆኖ በጨረታው ህግና ደንብ መሰረት ለሚመለከተው አካል እርምጃ እንዲወስድ ሪፖርት ተደርጎ ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ሊወስድ ይችላል፡፡
- ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሀሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ ወይም ከጨረታ እራስን ማግለል አይቻልም፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ላይ ማብራሪያ ወይም ማሻሻያ ጥያቄ ለግዥ ፈጻሚ አካል ማቅረብ የሚችሉት ጨረታው ከመከፈቱ 5 ቀናት በፊት መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታውን ሰነድ በ16ኛው አስራ ስድስተኛው የሥራ ቀን ከሆነ ብቻ ካልሆነ በሚቀጥለው በተመሳሳይ የሥራ ቀን ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ይታሸጋል፡፡ ጨረታው በዚያው ቀን ልክ 8፡00 ባለቤቱ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ጨረታው ሲከፈት የተጫራቾች ያለመሟላት የጨረታ ሂደቱን አያስተጓጉልም፡፡ ተጫራቾች ጨረታው በሚከፈትበት ዕለት ኦሪጅናል ዶክመንቶቻቸውን ይዘው መቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በገዙት ሰነድ ላይ ባለው ዋጋ ቫትን ጨምረው በግልጽ መሙላት አላባቸው። ተጫራቾች የጨረታ ቴክኒካልና ፋይናንሻል ዶክመንት የሚያቀርቡት፦ አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ ለእያንዳንዳቸው ቴክኒካልና ፋይናንሻል ዶከመንት በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል። የዋጋ መሙያ ስነዱ ስርዝ ድልዝ ካለው ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ ፡-
በስልክ ቁጥር 0961414894 /0925148317/0901557348/0924630260 በመደወል መረጃ መውሰድ የምችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
በደ/ኢ/ክ/መንግስት በኦሪ ዞን የደቡብ ኦሪ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
