በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር የሀዌላ ቱላ ክ/ከተማ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት መንገድ ትራንስፖርት ል/ጽ/ቤት በክ/ከተማ ውስጥ ባሉት ቀበሌያት ነባር መንገድ ጠረጋ እና የጠጠር ብተና ሥራ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር የሀዌላ ቱላ ክ/ከተማ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር የሀዌላ ቱላ ክ/ከተማ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት መንገድ ትራንስፖርት ል/ጽ/ቤት በክ/ከተማ ውስጥ ባሉት ቀበሌያት ነባር መንገድ ጠረጋ እና የጠጠር ብተና ሥራ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
የማሽነሪ ጥራት በተመለከተ፣
- የማሽነሪ ቴክኒክ ብቃት :- የቴክኒክ ብልሽት የሌለው የተሻለ ሞዴል የሆነ፤
- የሚጠቀመው ነዳጅ ዓይነት - ናፍጣ የሆነ፤
- በብልሽት ወቅት በአፋጣኝ ጥገና ማድረግ የሚችል ድርጅት፣
- በሰዓት የመሥራት አቅም ከፍ ያለ
የኪራይ ሁኔታ
- ሲኖ ትራክ በቢያጆ (16 ሜ.ኪ) ማቴሪያል መጫን የሚችል
- ግሬደር በሰዓት ሆኖ የነዳጅ ሁኔታ (ያለ ነዳጅ)
- ሲኖትራከ ከነ ነዳጅ ማቅረብ የሚችል፡፡
- የማሽነሪ አይነት - 1. ግሬደር ለጠጠር የማሽነሪ ዓይነት ብተና
2. ሲኖትራክ ጠጠር ለማጓጓዝ (16 ሜ/ኪ)
3. ሎቤድ ደርሶ መልስ ሲሆን
በዚሁ መሠረት በጨረታ መሳተፍ የምትፈልጉ መስፈርቱን የምታሟሉ ተጫራቾች፤
- በዘርፍ የተሰማሩ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው::
- የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቅት የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት፣ የዘመኑን ግብር ከፈሉበትን ታክስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- በአቅራቢዎች ዝርዝር ስለመመዝገባቸው የአቅራቢነት ምስክር ወረቅት ማቅረብ የሚችሉ።
- ከዚህ በፊት ከሰሩበት መንግስታዊ መስሪያ ቤት መልካም ስራ አፈፃፀም ማቅረብ የሚችል፡፡
- ሲኖ ትራክ እና ግሬደር የስሪት ዘመን እ.እ.አ 2012 እና ከዚያ በላይ ሆኖ የታደሰ ሊብሬ ማቅረብ የሚችሉ።
- ማንኛወም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) 30,000 (ሰላሳ ሺህ ብር) ወይም ቢድ ቦንድ ጋራንቲ እና Unconditional Credit Facility ማቅረብ የሚችል መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ በሀዌላ ቱላ ክ/ከተማ ገቢዎች ጽ/ቤት በመቅረብ የማይመለስ 200 /ሁለት መቶ ብር በመክፈልና ደረሰኝ በማምጣት ሰነዱን ከሀዌላ ቱላ ከ/ከተማ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 5 በመቅረብ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት (10) አስር ተከታታይ የስራ ቀናት እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ በግንባር በመቅረብ መግዛት ይቻላል፡፡
- የጨረታ ሰነዱ በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ተሞልቶ ኮፒና ኦርጅናል በመለየት በሰም በታሽገ ኤንቨሎፕ በተለያዩ ፖስታ አንድ ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ ቴክኒካልና ፋይናንሻል በመያዝ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በስራ ቀናት ቢሮ ቁጥር አምስት ግዥና ንብረት ሥራ ሂደት ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 10 የስራ ቀናት በ11ኛው ቀን ሲሆን የጨረታ ሳጥን በዚሁ እለት ከጠዋቱ 4፡00 ሠዓት ታሽጎ በ4፡30 ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡ የተገለፀው ቀን የእረፍት ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም ሕዝባዊ በዓላት ላይ የሚውል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመስረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስልክ ቁጥር ፡- 0916413290/0916864736
በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር የሀዌላ ቱላ ክ/ከተማ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት
