የኢትዮጵያ መድን ድርጅት አደጋ ደርሶባቸው ለደንበኞቹ ሙሉ የመድን ካሣ ከፍሎ የተረከባቸውን ቀረጥ የተከፈለባቸው፣ ልዩ ልዩ ተሽከርካሪዎች ልዩ ልዩ የተሽከርካሪ ውጫዊና የውስጥ አካላት እና የተለያዩ ብረታ ብረቶችን በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል፤
Ethiopian Insurance Corporation (የኢትዮጵያ መድን ድርጅት)
የጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ መድን ድርጅት አደጋ ደርሶባቸው ለደንበኞቹ ሙሉ የመድን ካሣ ከፍሎ የተረከባቸውን፡-
* ቀረጥ የተከፈለባቸው ልዩ ልዩ ተሽከርካሪዎች
* ልዩ ልዩ የተሽከርካሪ ውጫዊና የውስጥ አካላት፣
* የተለያዩ ብረታ ብረቶችን በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል፤
ማንኛውም የስም ማዛወሪያ፣ ተጨማሪ የጉምሩክ ቀረጥ፣ ግብር፣ እሴት ታክስና ሌሎች ወጪዎች ቢኖሩ ከፍሎ በጨረታ ለመግዛት የሚፈልግ ሁሉ ቃሊቲ ከራውን ሆቴል በስተጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ ሪከቨሪ ቴክኒክ ማዕከል በመገኘት ከህዳር 23 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ታህሳስ 7 ቀን 2017 ድረስ በመመልከትና የጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮጵያ መድን ድርጅት Ethiopian Insurance corporation/ ስም በተሰራ ሲፒኦ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ፡፡
ሀ/ የዕቃ ማስያዣ:- የጨረታ መነሻ ዋጋ 20 በመቶ ሲሆን ዝቅተኛ የዕቃ ማስያዣ ብር 1000 ነው::
ለ/ የተሽከርካሪ ማስያዣ
|
የጨረታ መነሻ |
እስከ ብር 50,000.00 |
20 በመቶ |
|
ከብር 50,000.00 |
እስከ ብር 100,000.00 |
ብር 15,000.00 |
|
ከብር 100,001.00 |
እስከ ብር 200,000.00 |
ብር 25,000.00 |
|
ከብር 200,001.00 |
እስከ ብር 300,000.00 |
ብር 37,000.00 |
|
ከብር 300,001.00 |
እስከ ብር 400,000.00 |
ብር 50,000.00 |
|
ከብር 400,001.00 |
እስከ ብር 500,000.00 |
ብር 60,000.00 |
|
ከብር 500,001.00 |
እስከ ብር 800,000.00 |
ብር 75,000.00 |
|
ከብር 800,001.00 |
ብር በላይ |
ብር 100,000.00 |
ተጫራቾች የሚገዙበትን ዋጋ ከተጨማሪ እሴት ታክስ በፊት በመሙላት የጨረታውን ሠነድ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ታህሳስ 7 ቀን 2017 ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት ጀምሮ እስከ ቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ ለገሀር በሚገኘው ዋናው መ/ቤት ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፤ ጨረታው ታህሳስ 8 ቀን 2017 ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ቃሊቲ በሚገኘው ሪከቨሪ ቴክኒክ ማዕከል ይከፈታል፡፡ በጨረታው ተሸናፊ ለሚሆኑ ተወዳዳሪዎች የጨረታ ማስከበሪያ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ከሁለት የሥራ ቀናት በኋላ ተመላሽ የሚደረግ ሲሆን ለአሸናፊዎች ግን ሂሳቡ በገዙት ንብረት ላይ የሚታሰብ ሆኖ የገዙትን ንብረት ተጫራቾች መክፈል ከጀመሩበት ቀን ጀምሮ በ10 ቀናት ጊዜ ውስጥ ክፍያ አጠናቀው ንብረቱን ባይረከቡ ለጨረታ ተሳትፎ ያስያዙት ገንዘብ በመቀጫ መልክ ለድርጅቱ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል፡፡ ክፍያ ፈፅመው ንብረቶቹን በተገለፀው ጊዜ የማያነሱ ተጫራቾች የጥበቃ ወጪ በቀን ብር 150 (አንድ መቶ ሃምሳ ብር) ይከፍላሉ።
ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ያሸነፈውን ተሽከርካሪም ሆነ ቁሳቁስ ባለበት ሁኔታ በአንድ ጊዜ ማንሳት አለበት።
ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር -
011 439-25-89 እና 011 439-25-45 መጠየቅ ይቻላል።
የኢትዮጵያ መድን ድርጅት
