Tender Detail

Tender Details

  • Company በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር በሜካ/ድ ዕዝ የ7ኛ ሚካ/ድ ክ/ጦር መምሪያ
  • Address ነቀምት ከተማ , ኢትዮጵያ, Phone: 0576604623
  • Website
  • Deadline20 Dec 2024, 9:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Food And Beverage

በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር በሜካ/ድ ዕዝ የ7ኛ ሚካድ ከ/ጦር መምሪያ ለ2017 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል ከዚህ በታች የተገለፁትን ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር በሜካ/ድ ዕዝ የ7ኛ ሚካ/ድ ክ/ጦር መምሪያ


የብሄራዊ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 01/2017

በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር በሜካ/ድ ዕዝ የ7ኛ ሚካድ ከ/ጦር መምሪያ ለ2017 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል ከዚህ በታች የተገለፁትን ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ሎት 1 የተለያዩ ዓይነት የፅህፈት ዕቃዎችን

ሎት 2 የተለያዩ ዓይነት ስልጠና መርጃ ዕቃዎችን

ሎት 3 የተለያዩ ዓይነት የህሙማን ቀለብ

ሎት 4 የተለያዩ ዓይነት የፅዳት ዕቃዎች

ሎት 5 የተለያዩ ዓይነት የተሽከርካሪ መለዋወጫ ዕድሳት ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በዚህም  መሰረት  ከሎት 1 እስከ  ሎት 5 ለተጠቀሱት  በዘርፉ  የተሰማሩ  ድርጅቶች፡-

  1. የታደሰ ንግድ ፈቃድና ምዝገባ ምስክር ወረቀት
  2. በዘርፉ የተሰማሩበት ንግድ ፍቃድ በዕቃ አቅራቢነት እና አገልግሎት በፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የተመዘገበ እና የግብር ከፋይ መለያ (TIN) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ተመዝጋቢ የሆነች
  3. ጨረታውን ለመሳተፍ በቅድሚያ ከተጠቀሱት ዕቃዎች የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን በምዕ/ዕዝ መምሪያ ግዥ ቢሮ በነቀምት ከተማ የቀድሞ ወጋገን ሆቴል በመቅረብ መግዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
  4. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዶቻቸውን ኦርጅናል እና ፎቶ ኮፒ ሰነድ ለየብቻው በታሸገ ኤንቨሎፕ አድርገው ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ተወዳዳሪ ድርጅቶች ናሙና የሚያስፈልገው ዕቃዎችን በመ/ቤቱ ፍላጎት መሰረት የማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡
  6. ተጫራቾች ለሚጫረቱባቸው ዕቃዎች አጠቃላይ ዋጋ ሎት 1 ብር 7,400.00 ሎት 2 ብር 7,400.00 ሎት 3 ብር 32,247,72 ፤ ሎት 4 ብር 35,894 88 ፤ ሎት 5 ብር 20,000.00 የጨረታ ዋስትና ቢያንስ ለስድስት ወር ፀንቶ የሚቆይ በባንክ የተረጋገጠ የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ እስከ ጨረታ መዝጊያ ቀን ድረስ ከዋና ሰነዱ ጋር በማያያዝ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
  7. ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ተከታታይ የስራ ቀናት ቅዳሜን ጨምሮ ታህሳስ 11/04/2017 ዓ/ም ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ 3፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ምዕ/ዕዝ ጠ/መምሪያ ግዥ ቢሮ በነቀምት ከተማ የቀድሞ ወጋገን ሆቴል አዳራሽ ውስጥ የሚከፈት ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው አለመገኘት የጨረታ አከፋፈት ስርዓቱን አያስተጎጉልም፡፡
  8. አሸናፊ ድርጅቶች ውል የሚፈርመው በምዕ/ዝ መምሪያ ግዥ ቢሮ በነቀምቴ ከተማ የቀድሞ ወጋገን ሆቴል ሲሆን ውል ከመፈረማቸው በፊት የወል ማስከበሪያ 10% በሲፒኦ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ያሸነፉበትን ዕቃ በራሳቸው ወጭ በማጓጓዝ እና በማራገፍ ለ7ኛ ሚካ/ድ ክ/ጦር ንብረት አስተዳደር ደዴሳ በተዘጋጀው ግምጃ ቤት ማስረከብ ግዴታ አለባቸው፡፡

ማሳሰቢያ ፡- የመንግስት መ/ቤቱ በጨረታ ሰነድ ውስጥ የተጠቀሱትን ዕቃዎች ካለው በጀትና የተሻለ መንገድ ካገኘ እንዲሁም በሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ የዕቃውን ብዛት 20% የመጨመር እና የመቀነስ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው።

ለተጨማሪ ማብራሪያ፡- ስልክ ቁጥር፡- 0576604623

 

በሀገር  መከላከያ  ሚኒስቴር  በሜካ/ድ  ዕዝ  የ7ኛ ሚካ/ድ ክ/ጦር  መምሪያ

 

Save Tender