የኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን መሠረታዊ ሠራተኛች ማኅበር ከሰኔ 30/2009 ዓ.ም እስከ ሰኔ 30/2016 ዓ.ም ያከናወናቸውን የሒሳብ ሥራዎች የውጪ ኦዲተሮችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ማንኛውም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶችን አሟልተው መወዳደር ይችላሉ፡፡
Chemical Industry Corporation (ኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ኬ.ኢ.ኮ/መሠማ/ጨ/01-2017
የኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን መሠረታዊ ሠራተኛች ማኅበር ከሰኔ 30/2009 ዓ.ም እስከ ሰኔ 30/2016 ዓ.ም ያከናወናቸውን የሒሳብ ሥራዎች የውጪ ኦዲተሮችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ማንኛውም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶችን አሟልተው መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ ለአስራ አምስት(15) ቀናት በአየር ላይ ይውላል፡፡ ጨረታው በአየር ላይ ከዋለበት ዕለት ጀምሮ ተወዳዳሪዎች ያዘጋጁትን የጨረታ ሠነድ ቦሌ ሩዋንዳ መንገድ አካባቢ ናሚቢያ ኢንባሲ ፊት ለፊት በሚገኘው የማኅበሩ ቢሮ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ከሰኞ እስከ አርብ ባለው የሥራ ቀናት ከጧቱ 2፡00 እስከ 6፡30 እና ከሰዓት በኋላ ከ7፡30 እስከ 10፡00 ባለው ጊዜ ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የማይመለስ ብር አንድ መቶ አስራ አምስት (ብር 115.00) በመክፈል ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ እየቀረቡ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ላይ የጨረታ ሳጥኑ የሚዘጋ ይሆናል፡፡ የጨረታ ሳጥኑ ከተዘጋ በኋላ የሚቀርብ የጨረታ መወዳደሪያ ሠነድ ተቀባይነት የለውም፡፡ 16ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይዘጋል፡፡
- ጨረታው በተዘጋበት ዕለት ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ ቦሌ ሩዋንዳ መንገድ አካባቢ ናሚቢያ ኢንባሲ ፊት ለፊት በሚገኘው የማኅበሩ ቢሮ ውስጥ የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ማኀበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ
09 13 73 69 09/09 12 02 63 38
09 14 33 16 66/0911 55 17 36
አዲስ አበባ
የኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን
