Tender Detail

Tender Details

  • Company በደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መንግስት የቤንች ሸኮ ዞን ሲዝ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
  • Address ደቡብ ፡ ኢትዯጵያ, Phone: 0477770620
  • Website
  • Deadline11 Dec 2024, 2:00 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Electronics Materials

በደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መንግስት የቤንች ሸኮ ዞን ሲዝ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት በ 2017 የበጀት አመት ለሴክተር መ/ቤቶች ዓመታዊ ልዩ ልዩ ግዢዎችን በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ መፈጸም ይፈልጋል፡፡

በደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መንግስት የቤንች ሸኮ ዞን ሲዝ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መንግስት የቤንች ሸኮ ዞን ሲዝ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት በ 2017 የበጀት አመት ለሴክተር መ/ቤቶች ዓመታዊ ልዩ ልዩ ግዢዎችን

በሎት 1 (አንድ) የጽህፈት መሳሪያ

በሎት 2 (ሁለት) የኤሌክትሮኒክስ

በሎት 3 (ሦስት) (ቧንቧ መለዋወጫ ዕቃዎች

በሎት 4 (አራት) ልዩ ልዩ የስፖርት ትጥቆችና ቁሳቁሶችን በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ግዢ መፈጸም ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በዘርፉ የተሰማሩትን አቅራቢ ድርጅቶች አወዳድሮ ግዢውን ለመፈጸም ይረዳን ዘንድ ከዚህ በታች በተዘረዘሩት የመወዳደሪያ መስፈርቶች እንድትወዳደሩ የሲዝ ከ/አስ/ር/ፋ/ጽ/ቤት ጥሪ ያቀርባል።

በዚህ  መሰረት፡-

የመወዳደሪያ  መስፈርቶች

  • በዘርፉ የተሰጠ ህጋዊና የታደሰ ፍቃድና የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉ
  • የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ
  • የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
  • የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ የሆነ
  • የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው
  • የጨረታ ማስከበሪያ የ10,000 (አስር ሺህ ብር) ሲፒኦ ከታወቀ ባንክ ወይም ኢንሹራንስ ማቅረብ
  • በጨረታው አሸናፊ ለሚሆኑበት የጽህፈት መሳሪያ፣ ኤሌከትሮኒከስ ፤ የቧንቧ መለዋወጫ ዕቃዎች እንዲሁም ልዩ ልዩ የስፖርት ትጥቅ እና የቁሳቁሶች ዓይነት ያሸነፉበትን ጠቅላላ ገንዘብ 10% የውል ማስከበሪያ ከታወቀ ባንከ ወይም ኢንሹራንስ ለማስያዝ ፍቃደኛ የሚሆን ማንኛውም በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

ማሳሰቢያ፡-

  • ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ጨረታው ለ 15 ተከታታይ ቀናቶች በአየር ላይ ቆይቶ በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዕለቱ 9፡30 ይከፈታል፡፡ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ተወካዮቻቸው ባሉበት በፋይናንስ ጽ/ቤት በግዢ ኬዝ ቲም ቢሮ ቁጥር-05 ይከፈታል፡፡
  • ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ሞልተው ሲመልሱ የፋይናንሻል አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ እንዲሁም የቴክኒካል አንድ ኦርጂናል እና ሁለት ኮፒ ማስረጃዎችን ለየብቻ በማሸግ የድርጅታቸውን ህጋዊ ማህተም በማድረግና ሁሉም ሰነዶች ላይ በመፈረም ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ቢሮ ቁጥር 05 ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
  • ተወዳዳሪዎች የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ከሲዝ ከተማ አስ/ር ገቢዎች ጽ/ቤት የማይመለስ 100 (አንድ መቶ) ብር በመክፈል ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
  • ተወዳዳሪ ድርጅቶች የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ለመግዛት ሲመጡ የንግድ ፍቃድ እና አቅራቢነት የምስክር ወረቀት ኮፒ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  • መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብት አለው።
  • ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0477770620 ወይም 09 11 452713 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ

 

በደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መንግስት የቤንች ሸኮ ዞን ሲዝ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት

Save Tender