ድርጅታችን አብዲ ጉዲና ኃላ/የተ/የፋይናንስ ህብረት ስራ ዩኒየን ዶልፊን ቫን (Dolphin Van) 2006 ሞዴል፣ ሲልቨር ከለር እና ጥሩ ይዞታ ያለውን ተሽከርካሪ በመነሻ ዋጋ ብር 3,600,000.00 (ሶስት ሚሊዮን ስድስት መቶ ሺህ ብር) ቫትን ጨምሮ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
አብዲ ጉዲና ኃ/የተ/ የፋይናንስ ህብረት ስራ ማኅበራት ዩኒየን
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር፡- AGFCU..01/2017
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ ዶልፊን ቫን (Dolphin Van) የመኪና ሽያጭ
ድርጅታችን አብዲ ጉዲና ኃላ/የተ/የፋይናንስ ህብረት ስራ ዩኒየን ዶልፊን ቫን (Dolphin Van) 2006 ሞዴል፣ ሲልቨር ከለር እና ጥሩ ይዞታ ያለውን ተሽከርካሪ በመነሻ ዋጋ ብር 3,600,000.00 (ሶስት ሚሊዮን ስድስት መቶ ሺህ ብር) ቫትን ጨምሮ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን መመዘኛዎች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።
- በጨረታው ለመሳተፍ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት በአዳማ ከተማ ከአለም ሆቴል ወደ አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በሚወስደው መንገድ 200 ሜትር ገባ ብሎ በሚገኘው የዩኒየኑ ቢሮ ከፋይናንስ እና ንብረት አስተዳደር ክፍል በአካል በመገኘት በማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ተሽከርካሪውን በድርጅቱ ህንፃ ፓርኪንግ ቦታ ቀርቦ መመልከት ይችላሉ፡፡
- ተጫራች ድርጅት ከሆነ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ አለበት፡፡ የሞሉት ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆኑን መግለጽ አለበት፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሞሉትን ዋጋ 5% በባንከ የተረጋገጠ CPO ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ቀናት አየር ላይ በመቆየት በ15ኛው ቀን ከቀኑ በ8:00 ሰዓት ተዘግቶ በ8:30 ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- በጨረታው አሸናፊ የሆነ ተጫራች ማሸነፉ ከተገለፀ ከ7 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ያሸነፈበት ዋጋ በሙሉ መክፈል ይኖርበታል፡፡ ሆኖም ሙሉ ክፍያ በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ መክፈል ከልቻለ ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ለዩኒየኑ ገቢ ይደረጋል፡፡
- ዩኒየኑ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አብዲ ጉዲና ኃ/የተ/ የፋይናንስ ህብረት ሥራ ማኅበራት ዩኒየን
