Tender Detail

Tender Details

  • Company ኤንዳ ኢትዮጵያ
  • Address አዲስ አበባ ከተማ ደብረዘይት መንገድ መስከረም ማዞሪያ 500 ሜትር ገባ ብሎ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-4-16-20-04
  • Website
  • Deadline02 Dec 2024, 10:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Vehicle

ኤንዳ ኢትዮጵያ ሲገለገልበት የነበረውን ቶዮታ ሃይሉክስ ደብል ካቢን ተሽከርካሪ ባለበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

ኤንዳ ኢትዮጵያ


የጨረታ ማስታወቂያ

ኤንዳ ኢትዮጵያ ሲገለገልበት የነበረውን ቶዮታ ሃይሉክስ ደብል ካቢን ተሽከርካሪ ባለበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም :-

  1. ማንኛውም ተጫራች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተሽከርካሪው በሚገኝበት አድራሻ ደብረዘይት መንገድ መስከረም ማዞሪያ 500 ሜትር ገባ ብሎ በሚገኘው በድርጅቱ ጽ/ቤት ከጠዋቱ 4፡00 እስከ 8፡00 ሰዓት ድረስ መመልከት ይችላሉ፡፡
  2. ተጫራቾች የሚገዙትን ተሸከርካሪ ጠቅላላ ዋጋ 20 በመቶ (20%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒአ (CPO) አሰርተው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ብቻ መሆን ይኖርበታል።
  3. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናው ለአሸናፊዎች ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብ ሲሆን ለተሸናፊዎች የጨረታው ውጤት እንደፀደቀ ይመለስላቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች የተሽከርካሪውን ዝርዝር የያዘው ሠነድ ላይ ተጫራቹ የሰጠው ዋጋ በሚለው አምድ /Column/ ሥር የሚገዙበትን ዋጋ በአሃዝና በፊደል ያለ ስርዝ ድልዝ ገልፀው በታሸገ ኤንቨሎፕ አዲስ አበባ ከተማ ደብረዘይት መንገድ መስከረም ማዞሪያ 500 ሜትር ገባ ብሎ በሚገኘው ኤንዳ ኢትዮጵያ ጽ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ነገር ግን የሚሰጡት ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለ ከጎኑ በተጫራቹ መፈረም አለበት፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ሰባት /7/ ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የጨረታውን ሰነድ ማስገባት አለባቸው፡፡
  6. አሸናፊ ተጫራቾች ጨረታውን ማሸነፋቸው ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ 5 ቀናት ውስጥ ገንዘቡን ገቢ በማድረግ በ 5 ቀናት ውሰጥ ንብረቱን የመረከብ ግዴታ አለባቸው፤ ይህ ካልሆነ ያስያዙት ገንዘብ ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል፡፡
  7. ተጫራቾች ከድርጅቱ ጽ/ቤት የተሽከርካሪውን ዝርዝር መረጃ የያዘ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ የማይመለስ 300 /ሶስት መቶ ብር/ እየከፈሉ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ሰባት /7/ ተከታታይ የስራ ቀናቶች ድረስ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  8. የጨረታ ሳጥኑ የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ሰባት /7/ የስራ ቀናት ከፍት ሆኖ በ7ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾቹ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ ጽ/ቤት ይከፈታል፡፡
  9. ተጫራቾች ስለአሻሻጡ ዝርዝር ሁኔታ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ከተያየዘው የተጫራቾች መመሪያ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  10. ድርጅቱ ለአሻሻጡ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፡- 011-4-16-20-04/09-11-10-08-60 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

 

ኤንዳ ኢትዮጵያ

 

Save Tender