Tender Detail

Tender Details

  • Company በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በምስራቅ ጎጃም መስተዳድር ዞን በባሶ ሊበን ወረዳ የጁቤ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት
  • Address ምስራቅ ጎጃም : አማራ ክልል ፡ ኢትዯጵያ, Phone: 0582460070
  • Website
  • Deadline25 Dec 2024, 9:30 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Office And Home Furniture

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በምስራቅ ጎጃም ዞን በባሶ ሊበን ወረዳ የጁቤ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት የግዥና ፋ/ን/አስ ቡድን የአዳራሽ ተገጣጣሚ /ተሳሳሪ/ የውጭ ስሪት ወንበር የቤትና የቢሮ እቃዎች ማስዋቢያዎችና መገልገያዎች አስመጭ የቤትና የቢሮ እቃዎች ማስዋቢያዎችና መገልገያዎች ችርቻሮ ንግድ እና የቤትና የቢሮ እቃዎች ማስዋቢያዎችና መገልገያዎች ጅምላ ንግድ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸውን ድርጅቶች በሎት አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በምስራቅ ጎጃም መስተዳድር ዞን በባሶ ሊበን ወረዳ የጁቤ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት


ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በምስራቅ ጎጃም ዞን በባሶ ሊበን ወረዳ የጁቤ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት የግዥና ፋ/ን/አስ ቡድን የአዳራሽ ተገጣጣሚ /ተሳሳሪ/ የውጭ ስሪት ወንበር የቤትና የቢሮ እቃዎች ማስዋቢያዎችና መገልገያዎች አስመጭ የቤትና የቢሮ እቃዎች ማስዋቢያዎችና መገልገያዎች ችርቻሮ ንግድ እና የቤትና የቢሮ እቃዎች ማስዋቢያዎችና መገልገያዎች ጅምላ ንግድ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸውን ድርጅቶች በሎት አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በጨረታው ለመሳተፍ የሚችሉ

  1. በየዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና ማቅረብ የሚችሉ ፤
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው እና የንግድ ምዝገባ ፈቃድ ያላቸው፤
  3. የተሞላው ዋጋ 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ በተጨማሪ እሴትታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ ፤
  4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱት ማስረጃዎችን የዋናውን ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ፤
  5. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ሙሉ አድራሻቸውን የሚገልፅ ክብ ማህተም፣ ፊርማ እና ቀን ማድረግ አለባቸው፣
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 1% /አንድ ፐርሰንት/ በC.P.O፣ በሁኔታ ላይ ያተመሰረተ የባንከ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ በሌተር ኦፍ ክሬዲት ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ የሚችሉ፣
  7. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 30 ቀን በአየር ላይ ውሎ በ31ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሠዓት ላይ የጫረታ ሳጥኑ ታሽጎ በዚሁ እለት ከጠዋቱ 4፡00 ሠዓት ላይ ተጫራቾች  ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 5 በግልጽ ይከፈታል፡፡ የመክፈቻ ቀኑ የበአል ቀን ከሆነ በቀጣይ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፣
  8. የጫረታ ሰነዱን የማይመለስ 400 /አራት መቶ/ ብር ከፍለው ከግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስ/ሂደት ከቢሮ ቁጥር 4 መግዛት ይችላሉ፡፡
  9. በጨረታ አሸናፊ የሆነው ድርጅት አሸናፊነቱ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ከ5 ተከታታይ የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ እና የወንበሩን ናሙና በማቅረብ ውል መፈፀም አለበት፡፡ በተገለፀው የጊዜ ገደብ ውስጥ ውል ያልፈጸመ እንደሆነ ለጨረታ ማስከበሪያ ያሲያዙትን ገንዘብ መ/ቤቱ ውርስ ያደርጋል ።
  10. አሸናፊው ተጫራች ወንበሩን የጁቤ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት ድረስ በማቅረብ ከአዳራሹ ወለል ጋር በብረትና በተሳሳሪ ቡለን በመግጠም ማስረከብ የሚችል፣
  11. ተጫራቾች በዋጋ መሙያው ቅፅ ላይ ዋጋው ሲሞላ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም። ስርዝ ድልዝ ካለው ፓራፍ መደረግ አለበት ::
  12. ተጫራች የሞሉትን የጨረታ ሰነድ ኦርጅናል በአንድ ፖስታ ፣ ኮፒ በአንድ ፖስታ ፣ C .P. O በአንድ ፖስታ በማሸግ እና 3ቱን ፖስታዎች በአንድ ትልቅ ፖስታ በሰም በማሸግ ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 5 በተዘጋጃው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ከ2፡30 እስከ 11፡30 ማስገባት ይኖረባቸዋል፤
  13. የመንግስት ግዥ መመሪያ እና አዋጅ ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ያላሟላ ተጫራች ከውድድር ውጪ ይደረጋል፡፡
  14. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0582460070

በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

 

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በምስራቅ ጎጃም መስተዳድር ዞን በባሶ ሊበን ወረዳ የጁቤ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት

Save Tender