Tender Detail

Tender Details

  • Deadline10 Dec 2024, 11:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Vehicle

የሀዲያ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች መኪናዎች፣ ትራከተሮች እና ሞተር ሳይከሎች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለፀው መሠረት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡


በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

የሀዲያ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች መኪናዎች፣ ትራክተሮች እና ሞተር ሳይከሎች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለፀው መሠረት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡

       ሎት 1 መኪናዎች

       ሎት 2 ሞተር ሳይከሎች

  1. ተሽከርካሪዎቹ የሚገኙበት አድራሻ ሀዲያ ዞን ፋይናንስ መምሪያ፣ ሀዲያ ዞን ጤና መምሪያ፣ ሀዲያ ዞን ፖሊስ መምሪያ እና ሀዲያ ዞን ግብርና መምሪያ ቅጥር ግቢ ውስጥ ይገኛሉ፡፡
  2. በተሽከርካሪዎች ጨረታ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ የሆነ ግለሰብ ወይም ድርጅት መሳተፍ ይችላል።
  3. ተጫራቾች ስለአሻሻጡ የተዘጋጀውን ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች የጨረታ መወዳደሪያ ሰነድና የዋጋ ማቅረቢያ ፎርም እና የተጫራቾች መመሪያ ጋዜጣው አየር ላይ ከዋለበት ቀን አንስቶ በተከታታይ 15/አስራ አምስት/ ቀናት ውስጥ በእያንዳንዱ ተሽከርካሪ በተናጠል፡- ሎት- መኪና ብር 400.00 /አራት መቶ ብር/ እና ሎት-2 ሞተር ሳይከል ብር 200.00/ሁለት መቶ ብር/ የማይመለስ ብር በመከፈል ከሀዲያ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዋና የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 17 በመቅረብ ዘወትር በሥራ ሰዓት ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የሚወዳደሩትን ተሸከርካሪ/ዎች በሎት በተናጠል ወይም በድምር የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የመነሻ ዋጋ 20% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ/CPO/ ብቻ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  5. የጨረታ መወዳደሪያ ዋጋ መሙያ መምሪያው ባዘጋጀው ፎርማት ላይ ብቻ በመሙላት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15/አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት የመወዳደሪያ ፖስታ አንድ ዋና /Original/ እና ቅጂ/Copy/ የጨረታ ሰነድ ለየብቻ በፖስታ ታሽጎና እንደገና ሁለቱም በአንድ ፖስታ ውስጥ ተካቶ በሰም በማሽግ ቢሮ ቁጥር 17 ላይ በሚገኘው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
  6. ማንኛውም ተጫራች በዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ ዋጋውን በግልጽ በአሃዝና በፊደል በመጻፍ በእያንዳንዱ በቀረበው ዋጋ ፊት ለፊት በፊርማ ማረጋገጥ አለባቸው፡፡ ያልተፈረመ ሰነድ ዋጋ አይኖረውም፡፡
  7. ተጫራቾች ለመግዛት የፈለጉትን ተሸከርካሪ/ዎች የጨረታ ዋስትና ካስያዙት ተሽከርካሪ/ ዎች ውጪ መወዳደር አይቻልም፡፡
  8. ተጫራቾች በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ መሠረት ከአንድ በላይ ተሽከርካሪ መጫረት ይችላሉ፡፡
  9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው አስራ ስድስተኛው/ ቀን ከጧቱ 5፡00 ሰዓት ላይ የጨረታ ሳጥን ታሽጎ በ5፡30 ሰዓት ላይ የሚከፈት ሲሆን ቀኑ የበዓል ወይም የዕረፍት ቀን ከሆነ በቀጣይ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ የሚከፈት መሆኑን እናሳውቃለን።
  10. ተጫራቾች በጨረታ ያሸነፉትን ተሽከርካሪዎች አሸናፊነታቸው በደብዳቤ በተገለጸ በ10 /አስር/ የስራ ቀናት ውስጥ ማንሳት አለባቸው ሆኖም በተጠቀሰው ቀናት ውስጥ ገዢው ካላነሳ ለሚደርሰው ለማንኛውም ችግር ሻጭ ተጠያቂ አይሆንም፡፡
  11. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ተሽከርካሪ ከመንግስት የሚፈለግ ግብርና ቀረጥ በሻጩ የሚሸፈን ይሆናል።
  12. አሸናፊው ተጫራች የተሸከርካሪ ስም ማዘዋወሪያ እና ሌሎች ልዩ ልዩ ወጪዎች በሙሉ በአሸናፊው ይሸፈናል፡፡
  13. ተጫራቾች የመነሻ ዋጋ እና የዋጋ ማቅረቢያ የጨረታ ስነድ አካል ሲሆን ከጨረታ ሰነድ ጋር የተያያዘ ነው፡፡
  14. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

ለበለጠ መረጃ - በስልከ ቁጥር ፡- 046-555-2337/2316 ደውሎ መጠየቅ የሚቻል መሆኑን እንገልጻለን፡

 

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የሀዲያ ዞን ፋይናንስ መምሪያ

Save Tender