Tender Detail

Tender Details

  • Deadline08 Dec 2024, 10:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Food And Beverage

የኢትዮጵያ ስራ አመራር ኢንስቲትዩት የህትመት ሥራዎች 1 የታሸጉና የፋብሪካ ውጤት የሆኑ ምግቦች ፣ ጥራጥሬና የእህል ውጤቶች እንዲሁም የአሣ ሥጋ የሚያቀርቡ ድርጅቶችን በጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡


 የጨረታ  ማስታወቂያ

   የጨረታ  ቁጥር 004/17

የኢትዮጵያ ስራ አመራር ኢንስቲትዩት የህትመት ሥራዎች 1 የታሸጉና የፋብሪካ ውጤት የሆኑ ምግቦች ፣ ጥራጥሬና የእህል ውጤቶች እንዲሁም የአሣ ሥጋ የሚያቀርቡ ድርጅቶችን በጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚወዳደሩ ድርጅቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው።

በዚህም መሰረት

  1. ተጫራቾች በዘርፋ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፤ የተጨማሪ እሴት ታከስ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ተፈላጊ ሰነዶች ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
  2. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀን ሲሆን ሰነድ የሚሸጠው በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከ2፡00 ሰዓት እስከ 11 ሰዓት የማይመለስ 100 /አንድ መቶ ብር/ አዲስ አባባ በሚገኘው ዋናው መ/ቤት 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 207 ሽያጭ ክፍል በመክፈል ደረሰኝ ይዘው ቢሮ ቁጥር 208 አቅርቦትና ኮንትራት አስተዳደር ቡድን ቢሮ በመምጣት ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
  3. የጨረታ ፖስታውን ፋይናንሻል እና ቅድመ መገምገሚያዎችን /ቴክኒካል ሰነድ/ በተለያየ ፖስታ ኦርጅናልና ኮፒ በማለት አሽጎ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን በየሎቱ /የጨረታ ሰነድ ላይ/ የተገለፀውን ብር በሲፒኦ ወይም በባንከ ዋስትና ከቴክኒካል /ህጋዊ ሰነዶች/ ኦርጅናል ሰነድ ጋር ወይም ለብቻው በፖስታ አሽጎ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  5. ይህ የጨረታ ደብዳቤ ወጪ ከተደረገበት ቀን ጀምሮ ለ15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀን በአየር ላይ ይውልና በ15ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን 4፡30 ተጨራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል፡፡
  6. የጨረታው መክፈቻ ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል ፡፡
  7. ተጋብዘው ፍቃደኛ በመሆን ሰነድ የመለሱ ድርጅቶች በተሰጣቸው ናሙና መሰረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  8. ኢንስቲትዩቱ ጨረታውን እንዳስፈላጊቱ በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡- አዲስ አበባ የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 ስልክ ቁጥር 0116-454147/0116-453598 /018-694931 ከሳሊህተ ምህረት ማርያም ቤ/ክርስትያን ፊት ለፊት የሚገኘው ህንፃ

 

የኢትዮጵያ ስራ አመራር ኢንስቲትዩት

Save Tender