በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ወሎ ዞን የወልዲያ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ለ2017 ዓ.ም በጀት አመት፣ የኤሌክትሪከና አጠቃላይ ጥገና መስሪያ መሳሪያዎች፣ የኤሌክትሪክ እቃዎች፣ የስፖርት እቃዎች ኳስ፤ የጽዳት እቃ፣ የጽህፈት መሳሪያ፣ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ተሽከርካሪዎችን የሚያስፈልጋቸውን ጥገና ለማስጠገን ጋራዦችን ለማወዳደር በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣው በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
Woldya College of Teachers Education (ወልዲያ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ወመትኮግዥ 7-1/38/2017
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ወሎ ዞን የወልዲያ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ለ2017 ዓ.ም በጀት አመት፣ የኤሌክትሪክና አጠቃላይ ጥገና መስሪያ መሳሪያዎች፣ የኤሌክትሪክ እቃዎች፣ የስፖርት እቃዎች ኳስ፤ የጽዳት እቃ፣ የጽህፈት መሳሪያ፣ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ተሽከርካሪዎችን የሚያስፈልጋቸውን ጥገና ለማስጠገን ጋራዦችን ለማወዳደር በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣው በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ በየስራ ዘርፋቸው ፈቃድ ያላቸው መሆን አለበት፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው::
- አሸናፊ ከሆኑ ወልዲያ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ድረስ በራሳቸው ወጪ ማስጫኛና ማውረጃ ችለው አጓጉዘው ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች አሸናፊነታቸው ከተገለፀላቸው ከ 5 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት ተከታታይ 5 ቀናት ውስጥ ቀርበው ውለታ መውሰድ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ያሸነፉትን እቃ አጠቃለው ካላስገቡ ምንም አይነት ክፍያ አይከፈልም።
- ተጫራች ከሞሉት 1% በባንከ ከተረጋገጠ cpo ወይም ጥሬ ገንዘብ በገቢ ደረሰኝ ማስያዝ እና ከጨረታ ፖስታ ውስጥ አብሮ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- በጨረታ ሰነዱ የተቀመጠውን የስራ ዝርዝር በጥንቃቄ መሙላትና ጠቅላላ ድምር በማስቀመጥ የሚሞሉትን ዋጋ የቫት ያካተተ መሆን ይኖርበታል ውድድሩም በየስራ ዘርፉ በሎት ነው፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአየር ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ ለ15 ቀን 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ገዝተው በመውሰድ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ኦርጅናልና ኮፒውን በመለየት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው የሚታሸገው ይህ ማስታወቂያ በአየር ከዋለበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ቀን መጨረሻ በ16ተኛው ቀን ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሆኖ ባይገኙ በመመሪያው መሰረት ጨረታው ይከፈታል። ተጫራቾች የሞሉትንና ያሸነፉበትን እቃ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ከጨረታ ሰነዱ ጋር አባሪ ሆኖ በቀረበው ማንኛውም ፎርም ዋጋ ማቅረቢያ ሰንጠረዥ /እስፔስፍኬሽን/ እንዲሁም የጨረታ ሰነዱ በታሸገበት ፖስታ ላይ ኦርጅናሉንም ሆነ ኮፒው ስማቸውን፣ ፊርማቸውን፣ የድርጅታቸውን ማህተምና ሙሉ አድራሻቸውን ሊነበብ በሚችል መልኩ ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል።
- የጨረታ መዝጊያ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ላቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ሌላ ለውጥ /ማሻሻያ/ ማድረግና ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
- እቃዎቹ በሙሉ ውድድሩ በሎት ነው፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት የመጨረሻው ቀን በዓልና ቅዳሜና እሁድ ቀን ከሆነ ወደ ሚቀጥለው የስራ ቀን እንደሚዞር ማወቅ፣ ጨረታው ከወጣ በኋላ የመከፈቻና የመዝጊያ ቀኑን ከመመሪያው ቀኑን የምናሳውቅ ሲሆን ግልጽ ያልሆነ ካለ በአድራሻችን በአካልም ይሁን በስልክ መጠየቅ ይቻላል።
- ተጫራቾች በራሳቸው ምክንያት ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ባይገኙ ያቀረቡት የጨረታ ሰነድ በመመሪያው መሰረት ባይገኙም በሌሉበት ይከፈታል፣
- የቫት ተመዝጋቢዎች የሆኑ እስከ ቫቱ ዋጋውን ሞልተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል ያልሞላ ተጫራች ቢኖር ከውድድሩ ይሰረዛል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 033-331-27-35
ደውለው መጠየቅ ይችላል፡፡
የወልዲያ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ
