ድርጅታችን ከዚህ በታች በሰንጠረዥ የተገለፁትን ክሬሸር እና አስፓልት ፕላንት ግዥ ለመፈጸም በዘርፉ የተሰማሩ አቅራቢ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የአማራ መንገድ ሥራዎች ድርጅት
ክሬሸር እና አስፓልት ፕላንት ግዥ ግልጽ ጨረታ
የጨረታ ቁጥር አመሥድ 05/2017
ድርጅታችን ከዚህ በታች በሰንጠረዥ የተገለፁትን ክሬሸር እና አስፓልት ፕላንት ግዥ ለመፈጸም በዘርፉ የተሰማሩ አቅራቢ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
|
ተ.ቁ |
የተሽከርካሪው አይነት
|
ብዛት
|
ክሬሽር እና አስፓልት ፕላንት የሚቀርቡበት ቦታ |
|
1. |
ከ80-100 ቶን አስፓልት ፕላንት
|
01 |
የጨረታ ሰነዱ ላይ በሚገለፅበት ቦታ ላይ |
|
2. |
ከ60-80 ቶን አስፓልት ፕላንት
|
01 |
የጨረታ ሰነዱ ላይ በሚገለፅበት ቦታ ላይ |
|
3. |
150-200 ክሬሸር
|
02 |
የጨረታ ሰነዱ ላይ በሚገለፅበት ቦታ ላይ |
ስለዚህ ከዚህ በታች የተገለፁትን የጨረታ መወዳደሪያ መስፈርቶችን የሚያሟላ ማንኛውም አቅራቢ ድርጅት በጨረታው መወዳደር ደችላል፡፡
-
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የተ.እ.ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና የግብር ከፋይነት ምዝገባ ሰርተፊኬት ቁጥር እና ግብር ስለመከፈላቸው የግብር ክሊራንስ ሰርተፊኬት ያላቸው መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚውል ሲፒኦ ወይም ያለቅድመ ሁኔታ እንደተጠየቀ የሚከፈል ባንክ ጋራንቲ ለእያንዳንዱ ከተራ ቁጥር 1-3 ለተዘረዘሩት ብር 500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ ብር) ለሶስቱም ከሆነ 1,500,000.00 (አንድ ሚሊዮን አምስት መቶ ሺህ ብር 00/00) ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ90 ቀን የሚቆይ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- መ/ቤቱ አሸናፊውን ተጫራች ድርጅት በሚመርጥበት ጊዜ የክሬሸር እና አስፓልት ፕላንቱን መጠን እንደአስፈላጊነቱ ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል፡፡
- ተጫራቾች ከላይ በሰንጠረዥ ለተገለጹት ተሽከርካሪዎች አስፈላጊ መረጃዎችን መጥቀስ እና ማያያዝ አለባቸው::
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ማለትም የዋጋ መሙያ ሰነዳቸውን ኮፒ እና ኦሪጅናል ለየብቻ እንዲሁም የቴክኒካል የመጫረቻ ሰነዳቸውን ማለትም የንግድ ስራ ፍቃድ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፊኬት፤ የግብር ከፋይ ሰርተፊኬት እና ሌሎች የክሬሸር እና የአስፓልት ፕላንት የቴክኒካል ሰነዶችን እና ሌሎች አስፈላጊ ዶክመንቶችን ኮፒ እና ኦሪጅናል ለየብቻ በተጨማሪም የጨረታ ማስከበሪያቸውን ከቴክኒካል ኦሪጅናል ሰነድ ጋር በማድረግ በአንድ በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 20 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ባሕርዳር ከተማ ከሚገኘው ዋና መ/ቤታችን አማራ መንገድ ሥራዎች ድርጅት አማራ ፓይፕ ፋብሪካ ፊት ለፊት ግዥ ኬዝ ቲም ቢሮ በመቅረብ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው በ20ኛው ቀን ከቀኑ 4:00 ተዘግቶ (ታሽጎ) በዚሁ ቀን 4:30 ይከፈታል፡፡ ይሁን እንጂ 20ኛው የመክፈቻ ቀን ከድርጅታችን የስራ ሰዓት ውጭ ከሆነ እና የመንግስት ካላንደር የሚዘጋው ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- በጨረታው ለተገለፁት ዕቃዎች ዝርዝር የጨረታ ሰነድ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል ከድርጅታችን ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 23 ቀርበው መግዛት ይችላሉ፡፡
- ድርጅታችን ምንም ዓይነት ቅድመ ክፍያን አይከፍልም፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058-320-35-76 መደወል ይችላሉ፡፡
አማራ መንገድ ሥራዎች ድርጅት
