ደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ የተለያዩ የፅህፈት ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
South Ethiopia Transport and Road bureau (የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ)
የፅህፈት ዕቃ ግዥ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 16/2017
ደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ የተለያዩ የፅህፈት ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሰረት፡
- ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፣ ዓመታዊ የስራ ግብር የከፈሉበትን፤ የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፊኬት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፊኬት ፎቶ ኮፒ አያይዘው የጨረታ ሰነድ ውስጥ በማድረግ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የዕቃዎችን ዝርዝር ስፔስፊኬሽንና የጨረታ ሰነድ ቢሮ ቁጥር 17 ድረስ መጥተው የማይመለስ ብር 50 /ሃምሳ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለ15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን ጨረታው በ15ኛው ቀን 11፡30 ሰዓት ታሽጎ በ16ኛው ቀን 4፡30 ላይ ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ነገር ግን 16ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከጠቅላላ ዋጋ 2% (ሁለት ፐርስት) በባንክ በተረጋገጠ /CPO/ በቼክ፣ በባንከ ጋራንቲ፣ በጥሬ ገንዘብ ገቢ በማድረግ በኦሪጅናል ሰነድ ውስጥ በፖስታ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ኦሪጅናልና አንድ ኮፒ እያንዳንዳቸው ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ እና ጠቅላላውን በአንድ በእናት ፖስታ ታሽጎ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ እስከ 11፡30 ድረስ ቢሮው ለዚሁ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የፅህፈት ዕቃ ዓይነት ናሙና የጨረታ ሰነድ ሲያስገቡ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጨማሪ መረጃ ከሰነዱ ማግኘት የሚቻል መሆኑን እያሳወቅን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የትራንሰፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ እንደገና በአዲስ መልክ በወጣው የግዢ አፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 70/2017 እና መመሪያው ላይ የተደረገውን ማብራሪያ ወይም ማሻሻያ ሰርኩላር ተፈጻሚ ይደረጋል።
ቢሮው ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለበለጠ ማብራሪያ፣ በስልክ ቁጥር 046 131 60 04 መደወል ይችላሉ
አድራሻ ዲላ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የትራንስፖርትና
መንገድ ልማት ቢሮ
