ዋልታ የገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየን ኃላፊነቱ የተወሰነ በ2017/18 ምርት ዘመን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በምስራቅ ጉራጌ ዞን ለሚገኙ ለአራት ገጠር ወረዳዎች እና ለሶስት ከተማ አስተዳደሮች እንዲሁም ለማረቆ ልዩ ወረዳ የአፈር ማዳበሪያ ስርጭት የሚያከናውኑ ህጋዊ የደረቅ ጭነት የትራንስፖርት ድርጅቶችን በጨረታ አወዳድሮ ከቡታጅራ ማዕከላዊ መጋዘን ወደ ገጠር ወረዳና ከተማ አስተዳደር ማሰራጫ ጣቢያዎች ማጓጓዝ ይፈልጋል፡፡
ዋልታ የገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየን ኃላ.የተወሰነ
የአፈር ማዳበሪያ ለማጓጓዝ ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ዋገዩ 002/2017
ዋልታ የገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየን ኃላፊነቱ የተወሰነ በ2017/18 ምርት ዘመን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በምስራቅ ጉራጌ ዞን ለሚገኙ ለአራት ገጠር ወረዳዎች እና ለሶስት ከተማ አስተዳደሮች እንዲሁም ለማረቆ ልዩ ወረዳ የአፈር ማዳበሪያ ስርጭት የሚያከናውኑ ህጋዊ የደረቅ ጭነት የትራንስፖርት ድርጅቶችን በጨረታ አወዳድሮ ከቡታጅራ ማዕከላዊ መጋዘን ወደ ገጠር ወረዳና ከተማ አስተዳደር ማሰራጫ ጣቢያዎች ማጓጓዝ ይፈልጋል፡፡
በዚህ መሰረት በጨረታ የሚሳተፉ ተጫራቾች ቀጥሎ የተዘረዘሩትን ግዴታዎች ማሟላት አለባቸው::
- በደረቅ ጭነት ትራንስፖርት ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማረጋገጫ የሚያቀርቡ መሆን አለባቸው፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የማይመለስ ብር 500 በመክፈል የጨረታውን ሰነድ ከዋልታ የገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየን ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ የዩኒየኑ ጽ/ቤት ድረስ በመቅረብ ዘወትር በስራ ሰዓት መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 300,000 /ሶስት መቶ ሺህ ብር/ /ሲፒኦ/ CPO/ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በገዙት የጨረታ ሰነድ ላይ ዋጋ ሞልተው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን እስከ ከቀኑ 8፡00 ድረስ በዋልታ የገበሬዎ ህብረት ስራ ዩኒየን ጽ/ቤት በመቅረብ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው በወጣ 10ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት በቡታጅራ ከተማ በዋልታ የገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየን ጽ/ቤት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻ በተገኙበት ይከፈታል፡፡ 10ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተገለጸው ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች በግዴታ ውስጥ የተካተቱትን ህጎች ማክበር የሚችል መሆን አለበት፡፡
- ዩኒየኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጨማሪ መረጃ ቢያስፈልግ በስልክ ቁጥር 0461151110/ 0916272305 / 0926854527 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
ዋልታ የገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየን ኃላ.የተወሰነ
ምስራቅ ጉራጌ ዞን
ቡታጅራ
