Tender Detail

Tender Details

  • Company በቤንሻንጉል ጉሙዝ ብሔራዊ ክልል መንግስት በመተከል ዞን የቡለን ከተማ ማዘጋጃ ቤት
  • Address ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል : ደቡብ ፡ ኢትዯጵያ, Phone: 09-10-40-23-39
  • Website
  • Deadline02 Dec 2024, 12:30 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Road And Bridge Construction

የቡለን ከተማ ማ/ቤት በ2017 በጀት አመት የቡለን ከተማ ውስጥ ለውስጥ መንገዶችን ለመክፈት እና የተበላሹ መንግዶችን ለመጠገን ማሽኖችን ማለትም ግሬደር፣ ሮሎ እና ዶዘር መከራየት ስለሚፈልግ ለመወዳደር የምትፈልጉ ተወዳዳሪዎች እንድትወዳደሩ ይጋብዛል።

በቤንሻንጉል ጉሙዝ ብሔራዊ ክልል መንግስት በመተከል ዞን የቡለን ከተማ ማዘጋጃ ቤት


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የቡለን ከተማ ማ/ቤት በ2017 በጀት አመት የቡለን ከተማ ውስጥ ለውስጥ መንገዶችን ለመክፈት እና የተበላሹ መንግዶችን ለመጠገን ማሽኖችን ማለትም ግሬደር፣ ሮሎ እና ዶዘር መከራየት ስለሚፈልግ ለመወዳደር የምትፈልጉ ተወዳዳሪዎች፦

1ኛ/ በዘርፉ (በማሸኖች ኪራይ) የተሰጠ አግባብነት ያለው የንግድ ፈቃድ እና የአቅራቢነት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው፡፡

2ኛ/ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያላቸው እና ማቅረብ የሚችሉ፡፡

3ኛ/ ተጫራቾች የተዘጋጀውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 ቀናት ውስጥ ከቡለን ከተማ ማ/ቤት የጨረታ ኮሚቴ በመቅረብ የስራው ዝርዝር መግለጫ እና የዋጋ መሙያ ሰነድ 200 (ሁለት መቶ ብር) በመከፈል መወዳደር ይችላሉ፡፡

4ኛ/ ተወዳዳሪዎች (ተጫራቾች) በሚያቀርቡት ስማቸው እና ሙሉ አድራሻቸውን በትክክል ጽፈው እና በመፈረም የድርጅቱን ክብ ማህተም በመምታት ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን አንስቶ ባሉት 10 የስራ ቀናት ብቻ ዋጋውን ሞልተው ማቅረብ የሚችሉ ሲሆን ጨረታው በ10ኛው ቀን 6:30 ሰዓት ተዘግቶ በ10ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ቡለን ከተማ ማ/ቤት ቢሮ ቁጥር-3 የሚከፈት ይሆናል፡፡

5ኛ/ ማ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

6ኛ/ ከዚህ በፊት ምንም አይነት የጥፋት ሪከርድ የሌለባቸው ቢሆን ይመረጣል፡፡

7ኛ/ ማሽኖቹ ብልሽት ቢገጥማቸው ከ5,000 ብር እና ከዚያ በታች ከሆነ በማ/ቤቱ በኩል የሚጠገን ሆኖ ከዚያ በላይ ከሆነ በድርጅቱ የሚጠገኑ ይሆናል፡፡

 

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡-09-10-40-23-39/ 09-15-52-26-31 ላይ

መደወል ይችላሉ፡፡

 

በቤንሻንጉል ጉሙዝ ብሔራዊ ክልል መንግስት በመተከል ዞን የቡለን

ከተማ ማዘጋጃ ቤት

Save Tender