የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ለመስክ አገልግሎት የሚውል ፒክ አጥ ዳ ጋቢና ተሽርካሪዎችን ከጨረታ ሰነዱ ጋር በተያያዘው ቴክኒካል መስፈርት መሠረት ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
Ethiopian Agricultural Businesses Corporation (የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን)
የመስክ ተሽከርካሪዎችን ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር ኢ.ግ.ሥ.ኮ/ብግጨ/07/2017
የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ለመስክ አገልግሎት የሚውል ፒክ አጥ ዳ ጋቢና ተሽርካሪዎችን ከጨረታ ሰነዱ ጋር በተያያዘው ቴክኒካል መስፈርት መሠረት ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ በዘርፉ ፈቃድ ያላችሁና የዘመኑን ግብር ለመክፈላችሁ ማስረጃ፤ የቫት ተመዝጋቢ፤ ቲን ፣ ከገቢዎች ክሊራንስ እና የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾች ዘወትር በሥራ ሰዓት ሳሪስ አቦ በሚገኘው ፋፋ የምግብ አ.ማ ጀርባ በሚገኘው የኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት ቢሮ ቁጥር 110 ቀርበው የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ። ተጫራቾች ለጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ 2% (እስከ አምስት መቶ ሸህ ብር ድረስ) በሲፒኦ ወይም በባንክ ጋራንቲ (unconditional) ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል። የጨረታው ዋጋ ለ90 ቀናት የጸና መሆን ይኖርበታል።
ጨረታው ህዳር 26 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮርፖሬሽኑ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል።
ኮርፖሬሽኑ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ፡
ስልክ ቁጥር፡- 011470-90-95 ወይም 0114-42-36-08
ፋክስ 0114-421312
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን
