ማህበራችን ፈጣን 3ኛ ደረጃ አገር አቋራጭ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶብስ የግል ባለንብረቶች ማህበር ጊዜያቸው ያበቃ ካዝናዎች፣ አሮጌ ብረታ ብረቶች እና ሌሎች ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
ፈጣን 3ኛ ደረጃ ከፍተኛ አገር አቋራጭ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ የግል ባለንብረቶች ማህበር
የጨረታ ማስታወቂያ
የንብረት ማስወገድ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
ማህበራችን ፈጣን 3ኛ ደረጃ አገር አቋራጭ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶብስ የግል ባለንብረቶች ማህበር ጊዜያቸው ያበቃ ካዝናዎች፣ አሮጌ ብረታ ብረቶች እና ሌሎች ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ማንኛውም ፍላጎት ያለው ተጫራች የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟላ ማንነቱን የሚገልጽ መታወቂያ ኮፒ በመያዝ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለሰነድ መግዣ የማይመለስ 50 ብር ብቻ በመከፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ቅዳሜን ጨምሮ ከፋይናንስና ግዢ ዳይሬከቶሬት ቡድን በመቅረብ ሠነዶቹን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ 5000 ( አምስት ሺህ ብር ) cpo ወይም በባንከ የተረጋገጠ ቢድ ቦንድ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል ::
- ተጫራቾች ማንነታቸውን የሚገልጽ መታወቂያ ኮፒና የሚወዳደሩበትን ዋጋ በአንድ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው የስራ ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ ለጨረታው ሰነድ ማስገቢያ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ያለባቸው ሲሆን የመክፈቻ ቀኑ እሁድ ወይም የበአል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ 4፡30 ላይ በመስሪያ ቤቱ የግዥ ቡድን ቢሮ ይከፈታል ፡
- የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ በጽሑፍ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ ባሉት በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ሙሉ ክፍያ ከፍሎ ንብረቶቹን ማንሳት ያለበት ሲሆን በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ባያነሳ ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ይወሰድበታል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች በሌላው ተጫራች ዋጋ ላይ ተመስርቶ ዋጋ ማስገባት አይችይልም፡፡
- ድርጅታችን ጨረታውን አስመልክቶ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፈልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ ፡- አውቶቢስ ተራ ትልቁ መናኸሪያ ውስጥ ቢሮ ቁጥር 4
ለበለጠ መረጃ 0112800343
ፈጣን 3ኛ ደረጃ አገር አቋራጭ የሕዝብ ማመላለሻ አዉቶብስ
የግል ባስንብረቶች ማህበር
