Tender Detail

Tender Details

  • Company የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ
  • Address ደቡብ ፡ ኢትዯጵያ, Phone: - - - - - -
  • Website
  • Deadline04 Dec 2024, 10:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Food And Beverage

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት ለደቡብ ኦሞ ስፖርት ማስልጠኛ ማዕከል ስፖርተኞች የሚውል የምግብ አቅርቦት ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ


የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት ለደቡብ ኦሞ ስፖርት ማስልጠኛ ማዕከል ስፖርተኞች የሚውል የምግብ አቅርቦት ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

1. የምግብ አቅርቦት ግዥ ለ25 ስፖርተኞች የሚሆን በጅንካ ከተማ ብቻ

በመሆኑም ተጫራቾች :-

  1. የዘመኑን ግብር የከፈሉና በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣
  3. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ ከብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ) በላይ ሲሆን የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የተመዝጋቢነት ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) እየከፈሉ ከመ/ቤቱ ግዢ ፋይናስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት መውሰድ ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ዋጋቸውን 10,000.00 (አስር ሺህ ብር ብቻ) በጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል። ጨረታው በአንድ ፖስታ የሚቀርብ ሲሆን አንድ ኦርጅናል እና አንድ ኮፒ መቅረብ አለበት:: ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በታሸገ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ባየር ላይ ውሎ በ16ተኛው ቀን 4:00 ሰዓት ድረስ በድርጅቱ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፣ እለቱ የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ በ4፡00 ሰአት ተዘግቶ በ4፡30 የሚከፈት ይሆናል፣
  6. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሃሣብ ላይ ስማቸውንና ፊርማቸውን፤ አድራሻቸውንና ስልክ ቁጥር ማስፈር አለባቸው፣
  7. የምግብ አቅርቦት በተመለከተ ለአንድ አመት ድረስ የሚቆይ ይሆናል፡፡
  8. መ/ቤቱ አሸናፊውን ተጫራች በሚመርጥበት ጊዜ የግዥውን ብዛት መጠን/ እንደአስፈላጊነቱ እስከ 20% ለመቀነስ / ለመጨመር / መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  9. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የምግብ አይነት መ/ቤቱ ባቀረበው የምግብ ሚኒ ዝርዝር መሰረት ብቻ ነው መወዳደር የሚችሉት ::
  10. ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ

Save Tender