የሀዋሳ ከተማ አስ/ፋ/ኢ/ል/መምሪያ በህዋላ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ በ2017 ዓ.ም ዓመት ዕቅድ መሠረት የከባድ ማሽነሪዎችና ተሽከርካሪ መለዋወጫ ዕቃዎችን አወዳድሮ በዘርፉ ፈቃድ ካለው አቅራቢ ድርጅት መካከል በጨረታ አወዳድሮ ግዥውን ለመፈጸም ይፈልጋል፡፡
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮ/ል/መምሪያ
በድጋሚ የወጣ ጨረታ ማስታወቂያ
የሀዋሳ ከተማ አስ/ፋ/ኢ/ል/መምሪያ በህዋላ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ በ2017 ዓ.ም ዓመት ዕቅድ መሠረት የከባድ ማሽነሪዎችና ተሽከርካሪ መለዋወጫ ዕቃዎችን አወዳድሮ በዘርፉ ፈቃድ ካለው አቅራቢ ድርጅት መካከል በጨረታ አወዳድሮ ግዥውን ለመፈጸም ይፈልጋል፡፡
በዚህ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅት መወዳደር ይችላሉ፡-
- በሥራ መስኩ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፤ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ :
- የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፣
- የጨረታ ሰነዱን ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይ/ኢኮ/ልማት መምሪያ ቢሮ (አዲሱ ከተማ አስተዳደር ህንፃ) አንደኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 10 ( አስር) በመቅረብ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 /ለአሥራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ ቀርባችሁ ሰነድ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ወስዶ ዋጋ ሞልቶ ማቅረብ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ (የተመሰከረ) ሲፒኦ (CPO) ወይም ቢድ ቦንድ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለበት፡፡
- ጨረታ ሰነዱ በሰም ለየብቻቸው በታሸገ ኤንቨሎፕ አንድ ኦሪጂናል እና ሁለት ኮፒ እና ፋይናንሻል በመያዝ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 (አሥራ አምስት) ተከታታይ ቀናት በፋይ/ ኢኮ/ልማ/ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 10 (ግዢ ኬዝ ቲም) ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በ16ኛው ቀን ከቀኑ 3፡00 ሰዓት ታሽጐ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትም ሆነ ባልተገኙበት ከቀኑ 3፡30 ሰዓት በቢሮ ቁጥር 10 ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን በበዓላት ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት የሚታሸግና የሚከፈትበት ቀን ይሆናል፡፡ የበዓል ቀን ከሆነ ደግሞ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስልክ ቁጥር ፡- 046-220-99-63/046-212-13-34
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ
