የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ከልል መንግስት ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ለ2017 በጀት አመት ለቢሮ ሥራ የሚያገለግሉ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ የእስቴሽነሪ እና የጽዳት ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 002/2017
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ከልል መንግስት ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ለ2017 በጀት አመት ለቢሮ ሥራ የሚያገለግሉ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ የእስቴሽነሪ እና የጽዳት ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ሎት 1 ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች
ሎት 2 የእስቴሽነሪ እና የጽዳት እቃዎች
በዚህም በመሰረት በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-
- የተጨማሪ እሴት ታክስ NAT/ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈለና አግባብ ያለው የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፡፡
- በፋይናንስ መስሪያ ቤቶች በዕቃ አቅራቢነት ዝርዝር የተመዘገቡና በህግ ያልተገደቡ፡፡
- የቲን ተመዝጋቢነት ምስክር ወረቀት ያለው፡፡
- ለእያንዳንዱ ዕቃ ግዥ ከቢሮ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት የቢሮ የግዥ/ ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 6 በመቅረብ የማይመለስ ብር 100.00 በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- የዕቃውን አይነት ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ የቴክኒካል የጨረታ ሰነድና የፋይናንስ የጨረታ ሰነድን ለብቻ ለብቻ ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን ለተዘጋጀ የቴከኒክና የፋይናንስ ሰነድ ተጨማሪ ተመሳሳይ አንድ አንድ ኮፒዎች አዘጋጅተው በኤንቨሎፕ የውጭ ገጽ ዋና ኦርጂናል/ወይም ኮፒ ብሎ በመፃፍ አሽገው ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- በማንኛውም ኤንቨሎፕ ውስጥ የጨረታ ማስከበሪያ/ማስገባት የለባቸውም ስለተጫራቾች የንግድ ፈቃድ የቫት ሰነድ መልካም አፈጻጸም ወዘተ መካተት ያለባቸው በቴክኒከ የጨረታ ሰነድ በሆኑት በዋናው ኦሪጅናል እና CV ኮፒ ተበሎ በተገለጹት በሁለቱም ኤንቨሎፕ ሲሆን በፋይናንስ የጨረታ ሰነድ በዋናው /ኦሪጅናል/ ሆኖ ኮፒ ኤንቨሎኘ ውስጥ ከፋይናንስ የጨረታ ሰነድ ውጪ ምንም ተጨማሪ መረጃ ማስገባት አይፈቀድም፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን የሚያስገቡበት የመጨረሻ ቀን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ዘወትር በስራ ሰዓት ለተከታታይ 15ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 በፊት ብቻ ይሆናል፡፡ ጨረታው በ15ኛው ቀን ከቀኑ በ8፡30 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት በ9:00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የቢሮ አዳራሻ በግልጽ ይከፈታል፡፡ ሆኖም 15ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው የሚዘጋውና የሚከፈተው በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓትና ቦታ ይሆናል ፡፡ማንኛውም የተጫራች ህጋዊ ወኪል በፍርድ ቤት የተረጋገጠና በኢፌዴሪ/ በክልሉ መንግስት ህጐች ተቀባይነት ያለው አሪጅናል የውከልና ሰነድ ይዞ መቅረብ አለበት ፎቶ ኮፒ ተደርጐ ብቻ የሚመጣ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ የሚያቀርቡት ለሚወዳደሩት ሎት ከጠቅላላ የጨረታ ዋጋ 2% ከታወቀ ባንክ በሚሰጥ የክፍያ ማዘዣ ቼክ ወይም ከታወቀ በባንክ ዋስትና የሚቀርብ በባንክ ዋስትና ለብቻው በታሸገ ፖስታ መሆን አለበት፡፡
- ጨረታውን በከፊል መጫረት የሚፈልግ ተጫራች ከተዘረዘሩት የዕቃ አይነቶች በአንድ ወይም ከአንድ በላይ መርጦ መጫረት ይቻላል፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ/ጉ አቅራቢ/ዎች /ተጨማሪ መረጃ የሚፈልጉ ከሆነ በቢሮ ስልክ ቁጥር 0113659360 ዘወትር በስራ ሰዓት መጠየቅ ይችላሉ፡፡
- ቢሮው ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
የቢሮው አድራሻ ፡- የጉራጌ ዞን አስተዳደር ጎን መሆኑን ጭምር እናሳውቃለን፡፡
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ
