የአብክመ ጤና ቢሮ አገልግሎት የሚውል የኤሌክትሮኒክስ እቃ ግዥ ከዚህ በታች የተዘረዘረውና በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ በግልፅ ጨረታ የግዥ ዘዴ ለመግዛት ይፈልጋል። በመሆኑም ተጫራቾች ከዚህ በታች በቀረበው ዝርዝር መሰረት የሚያቀርቡበትን ዋጋ ሞልቶ በመወዳደር አሸናፊ የሆነው ድርጅት ውል በመያዝ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።
Amhara Health Bureau (የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የአብክመ ጤና ቢሮ አገልግሎት የሚውል የኤሌክትሮኒክስ እቃ ግዥ ከዚህ በታች የተዘረዘረውና በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ በግልፅ ጨረታ የግዥ ዘዴ ለመግዛት ይፈልጋል። በመሆኑም ተጫራቾች ከዚህ በታች በቀረበው ዝርዝር መሰረት የሚያቀርቡበትን ዋጋ ሞልቶ በመወዳደር አሸናፊ የሆነው ድርጅት ውል በመያዝ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው።
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ሰርተፍኬት የሚያቀርብ።
- ከላይ በተ.ቁ 1-2 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ።
- የሚገዛው ዕቃ ጠቅላላ ዋጋ ከ200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ የሆነና የቫት ሰርተፍኬት ኮፒ ማስያዝ አለበት።
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ 80000.00 በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና የሚያስይዝ።
- ማንኛውም ተጫራች የመወዳደሪያ ሃሳቡን በታሸገ ፖስታ በጤና ቢሮ በግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ግዥ ክፍል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ 11፡30 ማስገባት ይችላሉ፤ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን 8:30 ታሸጎ 9:00 ይከፈታል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ ክፍል በጃይካ ህንፃ በ16ኛ ቀን 2017 ዓ.ም 8፡30 ታስጎ 9፡00 ሰዓት ይከፈታል። ሆኖም ዕለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በተከታዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚታሸግና የሚከፈት ይሆናል።
- ሌሎች ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።
- ቢሮው የግዥውን መጠን እስከ 2% ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ለእያንዳንዱ ሰነድ ብር 200.00 /ሁለት መቶ/ በመክፈል 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 213 ድረስ በአካል ቀርበው መግዛት ይቻላል።
- ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ስለ ጨረታው መረጃ ከፈለጉ በአብክመ ጤና ቢሮ ግዥ ክፍል ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0582221127 በመደወል ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ይቻላል።
- የጨረታው አሸናፊ የሆነ ድርጅት ያሸነፈበትን ዕቃዎች በራሱ ወጪ ክልል ጤና ቢሮ መጋዘን ድረስ ማቅረብ አለበት።
የአብክመ ጤና ቢሮ
ባህር ዳር
