የወላይታ ሶዶ ዳልጋ ከብት ዝርያ ማሻሻያ ማዕከል ምርታማ ያልሆኑ የጀርሲ ዝርያ ላሞችን እና የቦረና ዝርያ ጊደሮችን በጨረታ በመሸጥ ከማዕከሉ ለማስወገድ ይፈልጋል፡፡
የወላይታ ሶዶ ዳልጋ ከብት ዝርያ ማሻሻያ ማዕከል
የንብረት ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
የወላይታ ሶዶ ዳልጋ ከብት ዝርያ ማሻሻያ ማዕከል ምርታማ ያልሆኑ የጀርሲ ዝርያ ላሞችን እና የቦረና ዝርያ ጊደሮችን በጨረታ በመሸጥ ከማዕከሉ ለማስወገድ ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-
- በሽያጭ የሚወገዱ እንስሳትን መረጃ የያዘ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100/አንድ መቶ/ በመክፈል ይህ የንብረት ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከወላይታ ሶዶ ዳልጋ ከብት ዝርያ ማሻሻያ ማዕከል (ወላይታ ሶዶ) መግዛት የሚቻል መሆኑን፤ ንብረቶቹን በአካል ለማየት የሚፈልግ ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ከገዛበት ዕለት ጀምሮ ወደ ማዕከሉ በመምጣት ማየት የሚቻል ይሆናል።
- የመጫረቻ ሰነድ በፖስታ በማሸግ የጨረታ ሳጥን ከመታሸጉ በፊት በጨረታ ሳጥን መጨመር ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ሳጥኑ ወላይታ ሶዶ ዳልጋ ከብት ዝርያ ማሻሻያ ማዕከል (ወላይታ ሶዶ) ይገኛል፡፡
- ተጫራቾች የሚሰጡትን ዋጋ መነሻ በማድረግ 2% ሲ.ፒ.ኦ በባንከ የተረጋገጠውን ወይም ጥሬ ብር ማስያዝ የሚኖርባቸው ሲሆን አሽናፊዎች በውሉ መሠረት ያሸነፉትን ነጠላ ወይም ጥቅል ንብረት እስከሚያነሱ ድረስ ተይዞ ይቆያል፡፡ በጨረታው ተሸናፊዎች ያስያዙትን ሲ.ፒ.አ (ጥሬ ገንዘብ) ጨረታው ከተጠናቀቀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 /አምስት/ ቀናት ውስጥ ይመለስላቸዋል፡፡
- የንብረቶቹ መጫኛ፣ ማጓጓዣና ማውረጃ በአሸናፊው ድርጅት/ግለሰብ የሚሸፈን ሲሆን ንብረቶቹን የጨረታው አሸናፊ ውል ከገባበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 07 /ሰባት/ ቀናት ውስጥ ከማዕከሉ ሙሉ ክፍያ በመፈጸም ያነሳል፡፡
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት ጨረታ ሰነድ ላይ የተጫራቹን ሙሉ አድራሻ በግልጽ ማኖር አለባቸው።
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 ቀን ክፍት ሆኖ ይውልና በሚቀጥለው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው ቀን በ4፡00 ተዘግቶ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት እዛው የጨረታ ሳጥኑ ባለበት በወላይታ ሶዶ ዳልጋ ከብት ዝርያ ማሻሻያ ማዕከል (ወላይታ ሶዶ) ይከፈታል፡፡
- ማዕከሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በመሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ::
- ተጨማሪ መረጃ ቢያስፈልግ በስልከ 0916285340 ፤ 0911575873 እና 0461805744 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
የወላይታ ሶዶ ዳልጋ ከብት ዝርያ ማሻሻያ ማዕከል
