የኢትዮጵያ ስራ አመራር ኢንስቲትዩት ለዋና መ/ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ ማሻሻያ ግንባታና ፈርኒቸር አቅርቦ መግጠም ሥራን በዘርፍ ልምድ ያላቸውን ድርጅቶች አወዳድሮ ግዢ መፈፀም ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 003/17
የኢትዮጵያ ስራ አመራር ኢንስቲትዩት ለዋና መ/ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ ማሻሻያ ግንባታና ፈርኒቸር አቅርቦ መግጠም ሥራን በዘርፍ ልምድ ያላቸውን ድርጅቶች አወዳድሮ ግዢ መፈፀም ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም የሚወዳደሩ ድርጅቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው፡፡
በዚሁ መሰረት:-
- ተጫራቾች በህንፃ ግንባታ ለ2016 ዓ.ም. የታደሰ ደረጃ BC-4 እና ከዚያ በላይ የብቃት ማረጋገጫ ያላቸው ሆኖ፣ በዘርፋ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት ፣ የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ተፈላጊ ሰነዶች ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ የሚቆየው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 /ሃያ አንድ/ ተከታታይ ቀን ሲሆን ሰነድ የሚሸጠው በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከ2፡00 ሰዓት እስከ 11፡00 ሰዓት የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) አዲስ አበባ በሚገኘው ዋናው መ/ቤት 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 207 ሽያጭ ከፍል በመክፈል ደረሰኝ ይዘው ቢሮ ቁጥር 208 አቅርቦትና ኮንትራት ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ በመምጣት ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
- የጨረታውን ፖስታ ፋይናንሻል እና ቅድመ መገምገሚያዎችን /ቴክኒካል ሰነድ/ በተለያየ ፖስታ ኦርጅናልና ኮፒ በማለት አሸጎ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን የጨረታ ሰነድ ላይ የተገለፀውን ብር በሲፒኦ ወይም በባንክ ዋስትና ከቴክኒካል ህጋዊ ሰነዶች ኦርጅናል ሰነድ ጋር ወይም ለብቻው በፖስታ አሽጎ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 /ለሃያ አንድ/ ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ ቆይቶ በ21ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል፡፡
- የጨረታው መክፈቻ ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል፡፡
- ኢንስቲትዩቱ ጨረታውን እንደአስፈላጊነቱ በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡-
አዲስ አበባ የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 ስልክ ቁጥር 0116-454147/0116-453598/0118- 694931 ከሳሊህተ ምህረት ማርያም ቤ/ክርስትያን ፊት ለፊት የሚገኘው ህንፃ
የኢትዮጵያ ስራ አመራር ኢንስቲትዩት
