በሸገር ከተማ ገቢዎች ጽ/ቤት የገላን ጉዳ ክ/ከተማ ገቢዎች ጽ/ቤት የክ/ ከተማ ግብር/ታክስ ከፋይ የሆኑት ወ/ሮ Shenghua Xu የሚፈለግባቸውን የመንግስት ታክስ/ግብር ባለመከፈላቸው በኦሮሚያ ክልል ታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 203/2009 ዓ.ም አንቀፅ 43 በተሰጠው ሥልጣን መሰረት ያልተከፈለውን የመንግስት ታክስ/ግብር ለማስከፈል የታከስ ባለዕዳው ንብረት የሆነውን ለፋብሪካ አገልግሎት የሚውል ቤት ባለበት በሸገር ከተማ ገላን ጉዳ ክ/ከተማ ዳለቲ ወረዳ ቀበሌ 06 ያለውን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
Addis Ababa Revenues Bureau (የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ)
የጨረታ ማስታወቂያ
በሸገር ከተማ ገቢዎች ጽ/ቤት የገላን ጉዳ ክ/ከተማ ገቢዎች ጽ/ቤት የክ/ ከተማ ግብር/ታክስ ከፋይ የሆኑት ወ/ሮ Shenghua Xu የሚፈለግባቸውን የመንግስት ታክስ/ግብር ባለመከፈላቸው በኦሮሚያ ክልል ታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 203/2009 ዓ.ም አንቀፅ 43 በተሰጠው ሥልጣን መሰረት ያልተከፈለውን የመንግስት ታክስ/ግብር ለማስከፈል የታከስ ባለዕዳው ንብረት የሆነውን ለፋብሪካ አገልግሎት የሚውል ቤት ባለበት በሸገር ከተማ ገላን ጉዳ ክ/ከተማ ዳለቲ ወረዳ ቀበሌ 06 ያለውን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። በመሆኑም፡-
- ማንኛውም ዕድሜው ከ18 ዓመት በላይ የሆነ ሰው በጨረታው ለመሳተፍ የሚችል ሲሆን የንብረቱን መረጃ የሚያመለክት የጨረታ ሰነድ እና መመሪያ እንዲሁም የጨረታ ማቅረቢያ ቅፅ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 (አሥራ አምስት) ተከታታይ ቀናት የማይመለስ ብር 1000 (አንድ ሺህ ብር) ከገላን ጉዳ ክ/ከተማ ገቢዎች ጽ/ቤት ሠነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቹ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ እና በከለቻ ኦሮሚያ ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 (አሥራ አምስት) ቀናት ለሽያጭ የተዘጋጀውን ለፋብሪካ አገልግሎት የሚውል ቤት በሚገኝበት በሸገር ከተማ ገቢዎች ጽ/ቤት የገላን ጉዳ ክ/ከተማ ዳለቲ ወረዳ ቀበሌ 06 ካርታና ቁጥሩ L/000231/2007 የሆነውን ቤት በአካል በመገኘት መመልከት ይችላሉ፡፡
- የጨረታው መነሻ ዋጋ ብር 152,714,562 (አንድ መቶ አምሳ ሁለት ሚሊዮን ሰባት መቶ አስራ አራት ሺህ አምስት መቶ ስልሳ ሁለት) ብር ብቻ ይሆናል።
- ተጫራቹ ቤቱን ለመሸጥ ብር 300.000 የጨረታ ማስከበሪያ በማንኛውም ባንክ ክፍያ ማስያዣ ሲፒኦ (C.P.O) ማስያዝ ይኖርበታል።
- ተጫራቹ የቤቱን መረጃ በያዘው ሰነድ ላይ በዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ ላይ ተጫራቹ የሰጠው ዋጋ በአምድ (column) ሥር ቤቱን የሚገዛበትን ዋጋ በአኃዝ እና በፊደል ለይቶ በትክክል ጽፎ ከፈረሙ በኋላ በሰም የታሸገ ኤንቨሎፕ አድርጎ ለጫረታው በተዘጋጀ የጫረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ተጫራቹ አሸናፊ መሆኑ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ጨረታውን ያሸነፈበትን በቤቱን ዋጋ በ15 (አሥራ አምስት) ተከታታይ ቀናት ውስጥ ከፍለው ቤቱን የመረከብ ግዴታ አለበት፡፡ ከስም መዘዋወር ጋር የተያያዙ ወጭዎች በአሸናፊው ተጫራች ይሸፈናል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ወይም አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መበቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እና ታዛቢዎች በተገኙበት በገላን ጉዳ ክ/ከተማ ገቢዎች ጽ/ቤት ውስጥ በ15ኛው ቀን ከቀኑ 10፡00 ላይ ተዘግቶ በ16ኛው ቀን በ4፡00 ሠዓት ላይ ይከፈታል።
- ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0923382356 ወይም 0967986669 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
- ከስም መዘዋወር ጋር የተያያዙ ወጭዎች በአሸናፊው ተጫራች ይሸፈናል።
በሸገር ከተማ ገቢዎች አስተዳደር የገላን ጉዳ ክ/ከተማ ገቢዎች ጽ/ቤት
