በጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር NCB/04/2017 የኦሮሚያ መሬት ቢሮ ለመስሪያ ቤቱ የተለያዩ የቢሮ ዕቃዎች Scanner A-4, A3, Desk top, Lap top, External hard disc" ከህጋዊ ድርጅቶች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
Oromia Land Bureau (የኦሮሚያ መሬት ቢሮ)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር NCB/04/2017 የኦሮሚያ መሬት ቢሮ ለመስሪያ ቤቱ የተለያዩ የቢሮ ዕቃዎች Scanner A-4, A3, Desk top, Lap top, External hard disc" ከህጋዊ ድርጅቶች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ የሚከተለትን መሥፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል::
- ድርጅቶች የዘመኑን ግብር የከፈሉና ለተጨማሪ እሴት ታከስ የተመዘገቡበት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
- የጨረታው አሸናፊ ድርጅት በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ ዕቃውን ከመጋዘን (stock) ኖሮት ማቅረብ የሚችል።
- ተጫራቾች የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር / TIN NO/ ያላቸው መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር መግለጫ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት የማይመለስ 100 /አንድ ብር መቶ/ በመክፈል ከኦሮሚያ መሬት ቢሮ 3ኛ ፎቅ ፋይናንስ ክፍል መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ መሆን ይኖርባቸዋል።
- የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ CPO ለመወዳደር ላቀረቡት ጠቅላላ ዋጋ 250,000 (ሁለት መቶ ሃምሣ ሺህ ) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የእቃዎቹን የዋጋ ዝርዝር በጨረታ ማወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ስማቸውን፤ ፊርማቸውንና አድራሻቸውን በማስፈርና ማህተም በማድረግ የጨረታ ዶክመንት ኦርጅናልና ኮፒውን የፋይናንሻል እና ቲክኒካል ዶክመንት በተለያየ በታሸገ ኤንቨሎፕ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይም ባይገኙም ህዳር 27 ቀን 2017 በ7፡30 ሰዓት ተዘግቶ በ8፡00 ሰዓት ይከፈታል።
- የጨረታ ሣጥኑ ከታሸገ ወይም ከተከፈተ በኋላ የሚቀርብ ማንኛውም የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
- የጨረታው አሸናፊ አካል በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ ዕቃውን ጨርሶ ማስረከብ የሚችል።
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ
- ለተጨማሪ መረጃ
በዚህ ስልክ ቁጥር መጠቀም ይችላሉ 0910622700/0949445729/0919519951
አድራሻ ፡- ሳርቤት አደባባይን ዞሮ ወደ ቄራ መሄጃ ዋናው አስፋልት 200 ሜትር ላይ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት መስሪያ ቤቶች ቅጥር ግቢ ውስጥ
በኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት መስተዳደር የኦሮሚያ መሬት ቢሮ
