Tender Detail

Tender Details

  • Company በደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መንግስት የዳውሮ ዞን ታርጫ ከተማ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት
  • Address ዳውሮ ዞን ፡ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0912101978
  • Website
  • Deadline06 Dec 2024, 10:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Building Construction

በደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መንግስት የዳውሮ ዞን ታርጫ ከተማ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ለታርጫ ከተማ ማዘጋጃ ቤት በዋናው የአስፋልት መንገድ መሀል መብራት ዝርጋታ እና ግንባታ ሥራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።

በደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መንግስት የዳውሮ ዞን ታርጫ ከተማ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት


የአስፋልት  መንገድ  መሀል  መብራት  ዝርጋታ  እና

ግንባታ  ሥራ  ግልጽ  ጨረታ  ማስታወቂያ

በደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መንግስት የዳውሮ ዞን ታርጫ ከተማ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ለታርጫ ከተማ ማዘጋጃ ቤት በዋናው የአስፋልት መንገድ መሀል መብራት ዝርጋታ እና ግንባታ ሥራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል። ስለዚህ ማንኛዉም ተጫራች ማሟላት ያለባቸው

1ኛ.  

ከደረጃ 5- እና ከዚያ በላይ የኤሌክትሮ መካኒካል ሥራ ፈቃድ ያለው

2ኛ.  

በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያለው እና የአቅራቢዎች ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው፤

3ኛ.  

የታደሰ የሙያ ምዝገባ ፈቃድ ምስክር ወረቀት ያለው፣

4ኛ.  

የቫት/የተጨማሪ እሴት ታክስ እና የግብር ከፋይነት ቲን ተመዝጋቢ የሆነ፤

5ኛ.  

ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 21 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ከታርጫ ከተማ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ግ/ን/አስ/ር ቢሮ በመቅረብ ለዚህ አገልግሎት የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 500 /አምስት መቶ/ ብር በኢ/ን/ባ/አካውንት 1000042591738 ላይ ገቢ በማድረግ ከታ/ከ/አስ/ር ገቢዎች ቅ/ጽ/ቤት ደረሰኝ በመቀበል የጨረታ /ሠነዱን ከታ/ከ/አስ/ር ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት መውሰድ የሚችል፤

6ኛ.  

ተጫራቶች መ/ቤቱ ባዘጋጀው ፋይናንሻል ዋጋ መሙያ ሰነድ ኦርጂናሉንና የኦርጂናሉን ሁለት ኮፒ የቴክኒካል ሰነድ አርጂናሉንና የኦርጂናሉን ሁለት ኮፒ ኦርጂናሉን ኦርጂናል በማለት በአንድ እናት ፖስታ ውስጥ በመክተት የድርጅቱን ማህተም ስማቸዉን ፊርማቸዉንና አድራሻቸውን በግልጽ በማስፈር በሰም የታሸገ ፖስታ አዘጋጅተው ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ መክተት አለባቸው፤

7ኛ.  

ተጫራቾች የጨራታ ማስከበርያ ዋስትና /Bid bond/ 200.000 /ሁለት መቶ ሺህ/ ብር ብቻ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወይም ከሌሎች የግል ባንኮች የተረጋገጠ CPO ከኦርጅናል የቴክኒካል ዶክመንት ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸዉ፡፡

8ኛ.  

ተጫራቾች ካለፉበት ከጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ ገንዘብ በኢ/ን/ባ/ወይም ከሌሎች የግል ባንኮች የተረጋገጠ ዋስትና ማቅረብ አለባቸው፡፡

9ኛ.  

ተጫራቾች ለሚወስዱት ቅደመ-ክፍያ ገንዘብ ተመጣጣኝ ዋስትና ከኢትዮጵያ ንግድ ባንከ ወይም ከሌሎች የግል ባንኮች በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ዋስትና ማቅረብ አለባቸው፡፡ ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋስትና ከታወቀ የመድህን ድርጅት ሲሆን በከፍያ አፈፃፀም መመሪያ መሠረት ይሆናል።

10ኛ.  

ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ሲነበብ የነበረውና አርቲመትክ ቼክ ከተሰራ በኋላ ያለው ዋጋ ልዩነት ከ5% የበለጠ/ያነሰ ከሆነ ከጨረታው ውድቅ ይደረጋሉ፡፡

11ኛ.  

ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር በ22ኛው ቀን በ4:00 ሰዓት ታሽጎ በእለቱ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ዳውሮ ዞን ታርጫ ከተማ አስተዳደር ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ግቢ ግ/ፋ/ን/አስ/ር ቢሮ ውስጥ ይከፈታል፡፡ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ካልተገኙ የጨረታ መከፈት ሂደቱን እያስተጓጉልም ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡

12ኛ.  

ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያና መረጃ መጠየቅ ይችላሉ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 0912101978 እና 0910978256/ ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

ማሳሰብያ፡- ም/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

 

በደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መንግስት የዳውሮ ዞን ታርጫ

ከተማ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት

Save Tender