የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የተለያየ መጠን ያላቸውን ትራንስፎርመር ከአንድ ማከፋፈያ ጣቢያ ወደ ሌላ ማከፋፈያ ጣቢያ ለማንሳት፣ ለመጫን፣ ለማጓጓዝ እና ለማውረድ የሚውሉ የክሬን እና ሎቤድ ኪራይ አገልግሎት ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል። ስለሆነም ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ።
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር EEP/TSO/NCB/05/2017
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የተለያየ መጠን ያላቸውን ትራንስፎርመር ከአንድ ማከፋፈያ ጣቢያ ወደ ሌላ ማከፋፈያ ጣቢያ ለማንሳት፣ ለመጫን፣ ለማጓጓዝ እና ለማውረድ የሚውሉ የክሬን እና ሎቤድ ኪራይ አገልግሎት ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል። ስለሆነም ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ።
-
-
- ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በግዥ ኤጀንሲ የአቅራቢዎች ዝርዝር ድረ-ገጽ ላይ የተመዘገቡና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀን እና ሰዓት የካ ክ/ከተማ ወረዳ 9 ኮተቤ 02 ብረታ ብረት ፋብሪካ ፊትለፊት በሚገኘው ዋናው ፕሮኪዩርመንት ቢሮ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ የተመለከተውን የተሽከርካሪ ኪራይ ዋጋ ዝርዝር እና ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታ ቁጥር EEP/TSO/NCB/05/2017 የሚል ምልከት በማድረግ ከታች በተቀመጠው መሠረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
-
|
ተ.ቁ |
የአገልግሎት ዓይነት |
የጨረታ ማስከበሪያ ብር መጠን በሲፒኦ |
የጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት |
የጨረታው መክፈቻ ቀንና ሰዓት |
|
1 |
የክሬን እና ሎቤድ ተሽከርካሪ ኪራይ አገልግሎት |
250,000.00 |
ህዳር 23 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 |
ህዳር 23 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡15 |
- ገዥው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾች ሙሉ ዝርዝር መረጃውን ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት የሚችሉ ሲሆን ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ከፈለጉ ደግሞ ስልከ ቁጥር 011-5 58 19 16 /011-5 58 17 25 መደወል ይችላሉ።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል
