የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የተሽከርካሪ መለዋወጫ ለመኪና ጥገና ስራ የሚያገለግሉ የተለያዩ የኤሌክትሪክ እና ተዛማጅ ዕቃዎች ግዥ በጨረታ መለያ ቁጥር በድጋሚ ፌ.ቤ.ኮ/ብ.ግ.ጨ/ዕቃ/23/02/2017 ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ፌ.ቤ.ኮ/ብ.ግ.ጨ/ዕቃ/23/02/2017
- የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የተሽከርካሪ መለዋወጫ ለመኪና ጥገና ስራ የሚያገለግሉ የተለያዩ የኤሌክትሪክ እና ተዛማጅ ዕቃዎች ግዥ በጨረታ መለያ ቁጥር በድጋሚ ፌ.ቤ.ኮ/ብ.ግ.ጨ/ዕቃ/23/02/2017 ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- ኮርፖሬሽኑ ለሚያከናውነው የተሽከርካሪ መለዋወጫ ለመኪና ጥገና ስራ የሚያገለግሉ የተለያዩ የኤሌክትሪከ እና ተዛማጅ ዕቃዎች ግዥ ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውንና የዕቃውን ዋጋ በተለያዩ በታሸጉ ኤንቨሎፖች ማቅረብ አለባቸው፡፡
|
ሎት |
የግዥው ዓይነት |
የጨረታ ማስከበሪያ |
|
1 |
የተሽከርካሪ መለዋወጫ |
50,000 |
|
2 |
ለመኪና ጥገና ስራ የሚያገለግሉ የተለያዩ የኤሌክትሪክ እና ተዛማጅ ዕቃዎች |
20,000
|
- ጨረታው የሚከናወነው በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ሥነ-ሥርዓትና ይህንኑ አስመልክቶ በፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የግዥ መመሪያ መሠረት ሲሆን ከሚፈለገው ግዥ ጋር የተዛመደ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የግብር ከፋይ ማስረጃ የሚያቀርቡ መሆን ይኖርበታል።
- የተሟላ የአማርኛ የጨረታ ሰነዶችን ማንኛውም ፍላጎት ያለው ተጫራች ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 400.00 /አራት መቶ ብር/ በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ለገሀር በሚገኘው በተለምዶ የስነ-ምግባርና ፀረ- ሙስና ኮሚሽን ህንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 201 በኮርፖሬሽኑ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በአካል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቻቸውን በኮርፖሬሽኑ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 201 ለዚሁ ታሽጎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው በመጀመሪያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ወይም ህዳር 24 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ እንዲያቀርቡ ሆኖ በባንክ በተመሰከረለት ቢድ ቦንድ ወይም ሲፒኦ በፌዴራል ቤቶች ኮፖሬሽን ስም ከጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው። ዘግይቶ የቀረበ የጨረታ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል፤ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ህዳር 24 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡15 ሰዓት የኮርፖሬሽኑ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክተር ቢሮ ይከፈታል፡፡
- በሚያወጣው ፕሮግራም መሠረት አሸናፊው ተጫራች በኮርፖሬሽኑ በግንባር በመገኘት ዕቃውን ያስረክባል።
- ኮርፖሬሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ
በስልክ ቁጥር 011-855-36-17
የፓ.ሣ.ቁ. P.O BOX 299
የፌዴራል ቤቶች ኮርፓሬሽን
