በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ ለ2017 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ነገሮችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር A-03/2017
በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ ለ2017 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ፡
- የተለያዩ አይነት የተሽከርካሪ መለዋወጫ እቃዎች ዋጋው የሚሞላው በተናጠል ዋጋ ይሞላል።
- የተለያዩ አይነት የግንባታ እቃዎች ዋጋው የሚሞላው በተናጠል ዋጋ ይሞላል፡፡
- የቤቶች እድሳትና ጥገና ባህር ዳር መከላከያ ኮንዶሚንየም የሚታደስ፣ የሚጠገንና የሚሰራ ዋጋው የሚሞላው በሎት ዋጋ ይሞላል።
በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በዚህ ጨረታ መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች አግባብ ያለው የዘርፉ የታደሰ የዘመኑ የንግድ ፍቃድ የምዝገባ የምስክር ወረቀት የቫት ሰርተፍኬት፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፊኬት /TIN NO/ ከግብር ሰብሳቢ መስሪያ ቤት ግብር ስለመክፍላቸውና ጨረታ ለመሳተፍ የተፈቀደ መሆኑን የሚገልፅ ጊዜው ያላለፈበት ደብዳቤ /ማስረጃ/ ወይም የመጨረሻው ወር ወርሃዊ የቫት ሪፖርት ማቅረብ የሚችሉ ሆኖ፤ የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት ባህር ዳር ከተማ በሰ/ምዕ/ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ መኮድ ካምፕ ግዥ ቢሮ ቁጥር 02 በመምጣት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡ የጨረታ ማስከበሪያ/ BID BOND፣ CPO ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለበት፡፡ /GARANITE/ 1.የተለያዩ አይነት የተሽከርካሪ መለዋወጫ እቃዎች ብር 55.648.50 2.የተለያዩ አይነት የግንባታ እቃዎች፣ብር 192,733.20 3. የቤቶች እድሳትና ጥገና ባህር ዳር መከላከያ ኮንዶሚንየም የሚታደስ የሚጠገና የሚሰራ ብር 117,450.58 ጨረታው ከህዳር 05 ቀን 2017 ዓ/ም እስከ ህዳር 18 ቀን 2017 ዓ/ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት የጨረታ ሰነድ ተሸጦ የሚያልቅበት ቀን ሲሆን ህዳር 19 ቀን 2017 ዓ/ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከረፋዱ 4፡15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በባህር ዳር ከተማ በሰ/ምዕ/ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ መኮድ ዋናው ቢሮ አዳራሽ ወስጥ ይከፈታል።
- በጨረታው ላይ ያልተገለፁ ዝርዝር ሁኔታዎችን ከፈለጉ ቅፅ 1 ጥር 1998 ዓ/ም በአገር ውስጥ ለሚፈፀሙ እቃዎችና ተዛማች አገልግሎቶች ግዥ የሚውል መደበኛ የጨረታ ሰነድ ከገንዘብና የኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የመንግስት ግዥ ኤጀንሲ ድረ ገፅ ላይ ወይም ከመስሪያ ቤቱ በሚገዙት መደበኛ የጨረታ ሰነድ ማየት ይችላሉ፡
ስ.ቁ :- 0583216582/0583212892
የ ሰ/ምዕ/ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ
