የዝዋይ ተሃድሶ ልማት ማረሚያ ቤት በ2017ዓ/ም በጀት ዘመን ለህግ ታራሚዎች አገልግሎት የሚውል የሻይና ቡና ማፍያ ማሽን ፤ ለከብቶች ምግብ አገልግሎት የሚውል የቦንዳ ሳር : ለህግ ታራሚዎች ምግብ ዝግጅት የሚውል የበቆሎ ዱቄት እና ቀይ ሽንኩርት የሲቪል ሰራተኞች የእስፖርት ቱታ : የእስፖርት ጫማ ፣ ዶክተር ሹዝ እንዲሁም የተለያዩ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን የዝዋይ ተሃድሶ ልማት ማረሚያ ቤት ማዕከል
በድጋሚ የወጣ የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የዝዋይ ተሃድሶ ልማት ማረሚያ ቤት በ2017ዓ/ም በጀት ዘመን ለህግ ታራሚዎች አገልግሎት የሚውል የሻይና ቡና ማፍያ ማሽን ፤ ለከብቶች ምግብ አገልግሎት የሚውል የቦንዳ ሳር : ለህግ ታራሚዎች ምግብ ዝግጅት የሚውል የበቆሎ ዱቄት እና ቀይ ሽንኩርት የሲቪል ሰራተኞች የእስፖርት ቱታ : የእስፖርት ጫማ ፣ ዶክተር ሹዝ እንዲሁም የተለያዩ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ባሉት 15 ቀናት ውስጥ የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ሰነዱን ዝዋይ ተሃድሶ ልማት ማረሚያ ቤት ማዕከል ሁለተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 32 ከግዥ ክንውን ቡድን ከፍል በመግዛት በጨረታው ሰነድ ላይ የምትሸጡበትን ዋጋ በመግለፅ በሰም (በሙጫ) በታሸገ ኤንቨሎፕ በመሙላት በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በ15ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን 4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
- የተገለፀው ቀን ካላንደር የሚዘጋው ሆኖ ከተገኘ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ሰዓት የሚዘጋ እና የሚከፈት ይሆናል፡፡
ለመወዳደር የሚመጡ ተጫራቾች ፡-
- የጨረታ ማስከበሪያ ከሚያቀርቡት ዋጋ ተመጣጣኝ የሆነ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ ብር በባንክ በተመሰከረለት ቼክ /CPO/ብቻ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዞ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- አግባብነት ያለው የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፍቃድ የሚያቀርብ
- የዘመኑን የመንግስት ግብር ግዴታ መወጣታቸውን የሚገልፅ የድጋፍ ደብዳቤ የሚያቀርብ
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ የምስከር ወረቀት (ለሚያስፈልጋቸው ዕቃዎች) የሚያቀርብ
- በግዥ ኤጀንሲ ድረ-ገፅ (WWWppa.gov.et) የአቅራቢነት ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው የሚገልፅ የምስክር ወረቀት
- በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የድጋፍ ደብዳቤ
- ተጫራቾች ለሚጫረቱት እቃ ናሙና (sample) ለሚያስፈልጋቸው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ለሚጫረቱት እቃ በዘርፉ የተመዘገቡ መሆን አለባቸው፡፡
- ከላይ እንደተገለፀው ጨረታው በማዕከሉ ቅጥር ግቢ ሁለተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 32 ተጫራቾች እና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ ፡- በስልክ ቁጥር 0464414301 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
በፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን
የዝዋይ ተሃድሶ ልማት ማረሚያ ቤት ማዕከል
ዝዋይ
