የክርስቲያን በጎ አድራጎትና ልማት ማህበራት ህብረት (CCRDA) ከ50 ዓመታት በላይ በልማትና የበጎ አድራጎት ሥራ ላይ በማገልገል ላይ ይገኛል:: ድርጅቱ የተለያዩ ያገለገሉ የቢሮ እቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በዝግ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል::
Consortium of Christian Relief and Development Association (CCRDA) (የክርስቲያን በጎ አድራጎትና ልማት ማህበራት ህብረት)
ያገለገሉ እቃዎች ለመሸጥ በድጋሚ
የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የክርስቲያን በጎ አድራጎትና ልማት ማህበራት ህብረት (CCRDA) ከ50 ዓመታት በላይ በልማትና የበጎ አድራጎት ሥራ ላይ በማገልገል ላይ ይገኛል:: ድርጅቱ የተለያዩ ያገለገሉ የቢሮ እቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በዝግ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል:: እቃዎቹና የጨረታ ሰነዱ የሚገኙት ሃያ ሁለት የውሃ ልማት ቢሮ በስተጀርባ ጫካ ቡና አካባቢ በሚገኘው ትሪጎ ሆቴል ፊት ለፊት ባለው ሕንፃ አንደኛ ፎቅ ላይ IPHCE ቢሮ ነው:: ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አምስት ተከታታይ የሥራ ቀናትና ሰዓት እቃዎቹን ባሉበት ሁኔታ ተመልክተው ለጨረታው ባወጣው መመሪያ መሠረት መወዳደር ይችላሉ::
ጨረታውን ያሸነፈው ተጫራች ያሸነፈውን እቃ በአንድ ሳምንት ውስጥ ተረክቦ ማንሳት አለበት::
የክርስቲያን በጎ አድራጎትና ልማት ማህበራት ህብረት እቃዎቹን ለመሸጥ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
የክርስቲያን በጎ አድራጎትና ልማት ማህበራት ህብረት
አድራሻ :- ቃሊቲ ከአሽከርካሪዎችና መካኒኮች ማሰልጠኛ ማዕከል
ፊት ለፊት
ስልክ ቁጥር ፡- 0114-390322 ወይም 0114-393393
