Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Industrial Inputs Development Enterprise (የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት) (ኢኢግልድ)
  • Address በአራዳ ክፍለ ከተማ በወረዳ 02 ፒያሳ ከሊፋ ህንፃ አካባቢ በስተ ሰሜን አቅጣጫ የባቡር ሃዲዱን ተሻግሮ ወደ አራት መንታ በሚወስደው መንገድ ጣልያን ሰፈር (የቀድሞ ጅንአድ መ/ቤት) : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0111281529
  • Websitehttp://www.eiide.com.et/web/guest/about-us
  • Deadline28 Nov 2024, 10:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Industry And Factory

ድርጅታችን በአገር ውስጥ ለሚገኙ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካዎች ግብዓትነት የሚውል አንደኛ ደረጃ የተዳመጠ ጥጥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል::

Ethiopian Industrial Inputs Development Enterprise (የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት) (ኢኢግልድ)


የኢትዮጵያ  የኢንዱስትሪ  ግብዓቶች  ልማት  ድርጅት

 ለኢንዱስትሪ  ግብዓት  የሚውል  አንደኛ  ደረጃ  የተዳመጠ  ጥጥ  ግዥ

የጨረታ  ማስታወቂያ

   የጨረታ ቁጥር 005/2017

ድርጅታችን በአገር ውስጥ ለሚገኙ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካዎች ግብዓትነት የሚውል አንደኛ ደረጃ የተዳመጠ ጥጥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል::

  1. በዘርፉ የታደስ ንግድ ሥራ ፍቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፍኬት፤ የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸው የሚያረጋግጥ ክሊራንስ፣ የግብር ከፋይነት ምዝገባ ሠርተፍኬት ያላቸው በግዥ ኤጀንሲ የ እቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆን ይገባቸዋል::
  2. ለጨረታ የተዘጋጀውን ዝርዝር የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ፒያሳ ከሊፋ ህንፃ ፊት ለፊት ቢስ መብራት ከሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ በመቅረብ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ጠዋት 2፡00-6፡30 ከሰዓት 7፡30 እስከ 11፡00 መግዛት ይችላሉ::
  3. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ብር 500,000.00 (አምስት መቶ ሺ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (ሲ.ፒ.ኦ) ብቻ ለብቻው በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
  4. የጨረታ መወዳደሪያ ዋጋቸውንና ከላይ ከተጠቀሱት ህጋዊ ሠነዶች ጋር በታሸገ ኤንቨሎፕ አንድ ኦሪጅናል እንዲሁም አንድ ኮፒ በማድረግ እስከ ህዳር 19 ቀን 2017 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ድረስ በኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብአቶች ልማት ድርጅት የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ማቅረብ ይችላሉ:: ከጨረታው መዝጊያ በኃላ የሚቀርብ ሰነድ ተቀባይነት የለውም::
  5. ጨረታው በተመሳሳይ ቀን ኅዳር 19 ቀን 2017 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡10 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል::

ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ እንዲሁም ለማህበረሰቡ ይጠቅማሉ ያላቸውን ውሳኔዎች የመወሰን መብቱ የተጠበቀ ነው::

የኢትዮጵያ  የኢንዱስትሪ  ግብዓቶች  ልማት  ድርጅት

ለበለጠ  መረጃ  በስልክ  ቁጥር  0113-69-22-43/69-18-86

Save Tender