በመከላከያ ሰራዊት ፋውንዴሽን ስር የሚገኙ የቀላል ተሽከርካሪዎች ጥገና እድሳት አገልግሎት ግዥ በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡
የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን
የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር ፡- መ.ሠ.ፋ/ብ.ግ.ጨ-03/2017 ዓ/ም
በመከላከያ ሰራዊት ፋውንዴሽን ስር የሚገኙ የቀላል ተሽከርካሪዎች ጥገና እድሳት አገልግሎት ግዥ በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡
በመሆኑም ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ድርጅቶች በጨረታ እንዲሣተፉ ይጋብዛል፡፡
- ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉና በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር) TIN/፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሠርተፊኬት እና የአምራችነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል ።
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የጨረታ ሰነዱን አዲስ አበባ ቂርቆስ ክ/ከተማ ከሜክሲኮ ወደቄራ በሚወስደው መንገድ ላንድማርክ ሆስፒታል ጎን በሚገኘው በፋውንዴሽኑ ዋና መ/ቤት ግዥ ቡድን በስራ ሰዓት በመቅረብ የማይመለስ ብር 1000.00 (አንድ ሺ ብር) በመክፈል ሠነዱን ማግኘት ይችላሉ፡፡ የጨረታው ቴከኒካል እና የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ በ16ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በፋውንዴሽኑ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ቴክኒካል ሰነድ ይከፈታል፡፡ ነገር ግን 16ኛው ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል፡፡ ስለ ጨረታው ዝርዝር ሁኔታ ከጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የቴክኒክ እና የፋይናንሻል የጨረታ ሰነድ አንድ ኦርጅናል እና አንድ ኮፒ ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ማስከበሪያ ዋስትና ለሎት አንድ (በናፍጣ ለሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ብር 50,000.00 ለሎት ሁለት (በቤንዚል ለሚሰሩ ተሽከርካሪዎች) ብር 50,000.00 በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ/C.P.O / ወይም በባንክ ጋራንቲ ከጨረታ ቴክኒካል ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ።
አድራሻ፡- ከቄራ ወደ ሜክሲኮ በሚወስደው መንገድ ላንድማርክ ሆስፒታል ጎን
ስ.ቁጥር 011 557 2734
ፓ.ሣ.ቁ.5680
አዲስ አበባ
የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን
