Tender Detail

Tender Details

  • Deadline26 Nov 2024, 10:30 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Metals And Metal Working

የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ለኮርፖሬሽኑ አገልግሎት እየሰጡ ለሚገኙ ቀላልና ከባድ ተሽከርካሪዎች የተለያዩ መለዋወጫ እቃዎች ግዥ እና ሰበር ስፖቦዳ መስሪያ የሚያግለግሉ የተለያዩ ብረታ ብረቶች ግዥ ለመፈጸም በዘርፉ የተሰማሩ አቅራቢዎችን በጨረታ ማወዳደር ይፈልጋል፡፡


 

ግልጽ  የጨረታ  ማስታወቂያ

የጨረታ  ቁጥር ፡- ኢንሥኮ  ማእከል  ግዥ /17 05/2017

የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ለኮርፖሬሽኑ አገልግሎት እየሰጡ ለሚገኙ ቀላልና ከባድ ተሽከርካሪዎች የተለያዩ መለዋወጫ እቃዎች ግዥ እና ሰበር ስፖቦዳ መስሪያ የሚያግለግሉ የተለያዩ ብረታ ብረቶች ግዥ ለመፈጸም በዘርፉ የተሰማሩ አቅራቢዎችን በጨረታ ማወዳደር ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም በጨረታ ላይ መወዳደር የሚፈልጉ ድርጅቶች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መመዘኛዎች ማሟላት አለባቸው፡፡ ቀላልና ከባድ ተሽከርካሪዎች የተለያዩ መለዋወጫ እቃዎች ግዥ እና ሰበር ስፖቦዳ መስሪያ የሚያገለግሉ የተለያዩ ብረታ ብረቶች ግዥ

  1. ተጫራቾች በዘርፉ ለ2016/2017 በጀት ዓመት የታደሰ የንግድ ፈቃድ/ ጨረታው እስከሚከፈትበት ቀን ድረስ ሊያገለግል የሚችል የንግድ ስራ ፈቃድ ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ፣ የአቅራቢነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የተሰጠ ወቅታዊ ክሊራንስ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት እና የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት /TIN/ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ እነዚህ ሰነዶች በቴክኒካል ፕሮፖዛል ፖስታ ውስጥ ታሽገው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. ተጫራቾች ከላይ የተገለጹትን ሰነዶች ከጨረታ ሰነድ ማቅረቢያው ቀነ ገደብ በፊት ማቅረብ አለባቸው::
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 450.00 (አራት መቶ አምሳ ብር) በመክፈል ከኅዳር 2 /2017 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ ከጠዋቱ 2፡00-6፡00 ሰዓት እንዲሁም ከሰዓት ከ7፡00-10:30 ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡00-6፡00 ሰዓት ድረስ ማዕከል ግዥ ዋና ክፍል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን እስከ ጨረታው መዝጊያ ዕለት እስከ ኅዳር 17 /2017 ከጠዋቱ 4፡30 ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች ከላይ ለተጠቀሰው ጨረታ የጨረታ ማስከበሪያ : ብር 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር) በጥሬ ገንዘብ፣ በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ስም አሰርተው ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡ ኢንሹራንስ ቦንድና ቼከ ተቀባይነት የላቸውም፡፡ የጨረታ ማስከበሪያው ፖስታ ውስጥ ወይም ለብቻው ታሽጎ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  6. ተጫራቾች የቴከኒክ መወዳደሪያ ሰነዳቸውን እና ዋጋ የሞሉበትን የጨረታ መወዳደሪያ ሀሳባቸውን በግልጽ ከፋፍለው በተለያየ ኤንቨሎፕ በማሸግና ኮፒ እና ኦሪጅናል በማለት ኅዳር 17 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ዋናው መ/ ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ አድራሻ ከታች ተገልጿል፡፡
  7. ከዋና የመወዳደሪያ ሀሳብ (ኦሪጅናል) በተጨማሪ የሚፈለጉ ኮፒዎች አንድ የቴክኒካል ሰነድ ኮፒ እና አንድ የፋይናንሻል ሰነድ ኮፒ ነው::
  8. በቴክኒከ ግምገማ እና በፋይናንስ ግምግማ ተደርጎ አሸናፊ የሆነው ድርጅት ተመራጭ ይደረጋል፡፡
  9. አሸናፊው ድርጅት የውል ማስከበሪያ መጠን ለአሸነፉበት እቃ ጠቅላላ ዋጋ 10 ፐርሰንት በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና በኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ስም አሰርተው ውሉን የሚፈጽሙ ይሆናል፡፡
  10. ኮርፖሬሽኑ ጨረታውን በከፊልም ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

ለማንኛውም ማብራሪያ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡

ለተጨማሪ መረጃ፡- ስልክ ቁጥር 011 416 7345/0114 669 336 በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡

አድራሻ ፡- ደብረዘይት በሚወስደው መንገድ በቅሎ ቤት ከዳሸን ባንከ ዋናው መስሪያ ቤት ፊት ለፊት

 

የኢትዮጵያ  ንግድ  ሥራዎች  ኮርፖሬሽን

Save Tender