የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሰሜን ምስራቅ አዲስ አበባ ዲስትሪከት የባንኩ ንብረት የሆኑ የሶፋና የመጋረጃ ጨርቅ ማምረቻ ማሽኖችን ከሸገር ከተማ፤ ሱሉልታ ወረዳ በማንሳት (በመንቀል) እስከ ገላን ከተማ ድረስ የመንቀልና የማጓጓዝ ስራ የሚሰሩ ድርጅቶችን ግለሰቦችን በጨረታ ማወዳደር ይፈልጋል፡፡
Development Bank of Ethiopia (የኢትዮጵያ ልማት ባንክ)
ማሽን የመንቀልና የማጓጓዝ
ስራ ጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሰሜን ምስራቅ አዲስ አበባ ዲስትሪከት የባንኩ ንብረት የሆኑ የሶፋና የመጋረጃ ጨርቅ ማምረቻ ማሽኖችን ከሸገር ከተማ፤ ሱሉልታ ወረዳ በማንሳት (በመንቀል) እስከ ገላን ከተማ ድረስ የመንቀልና የማጓጓዝ ስራ የሚሰሩ ድርጅቶችን ግለሰቦችን በጨረታ ማወዳደር ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ስራውን መስራት የምትፈልጉ እና የሚከተለውን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው ላይ እንድትሳተፉ ተጋብዛችኋል፡፡
- የኤሌክትሮ መካኒካል ወይም በተመሳሳይ ሙያ ዘርፍ አገልግሎት የመስጠት፤ ማሽን የመትከል እና የማንሳት መንቀል/ የሙያ ፈቃድና የስራ ልምድ ማቅረብ የምትችሉ ፤
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ምዝገባ እና የንግድ ስራ ፍቃድ ሰርተፍኬት ያላቸው እንዲሁም የዘመኑ ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው
- የቲን ሰርተፍኬት ያላቸው እና ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፤
- ስራውን ሊሰሩ ያሰቡበት መንገድ የሚተነትን እቅድ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ በዚሁ መሰረት ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች እንዲሁም የማጓጓዣ ዋጋ በማካተት እስከ ህዳር 16 ቀን 2017 ዓ.ም 11፡00 ሰዓት ድረስ በዲስትሪክቱ ቢሮ በመገኘት ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ጨረታው የሚከፈተው ህዳር 17 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ሰሜን ምስራቅ አዲስ አበባ ዲስትሪክት ቢሮ ሲሆን አሸናፊው ከተገለጸበት ጀምሮ በ1 ቀን ውስጥ በባንኩ በመቅረብ የግዴታ ውል መፈረም አለበት፡፡ ስራውን መስራት የምትፈልጉ እና መስፈርቱን የምታሟሉ ተጫራቾች ህዳር 11 እና ህዳር 12 ቀን 2017 ዓ.ም በአካል በመገኘት የሚነሱ ማሽኖችን መጎብኘት የሚቻል ሲሆን በተጨማሪም የሚነቀሉትንና የሚጓጓዙትን ማሽኖች ዝርዝር መረጃዎች ከዲስትሪክቱ ቢሮ ማግኘት የሚቻል መሆኑን እንገልጻለን፡፡ ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ በሙሉም ሆነ በከፊል ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
አድራሻ፡- ካዛንቺስ ሾንጌ ህንጻ 1ኛ ፎቅ
ለበለጠ መረጃ ስ.ቁ 0115 57 72 33
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሰሜን ምስራቅ አዲስ አበባ ዲስትሪክት
