በኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ቃሊቲ ኦፕሬሽን ትራኪንግ በ2017 ዓ.ም ለጋራዥ የሚያስፈልጉ የተለያዩ ቁሳቁሶች ግዥ (different types of Garage Equipment's for Heavy Trucks) በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ የቃሊቲ ትራኪንግ ቅ/ጽ/ቤት
ብሔራዊ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር ESL/KOT/NCB/G/DTGE/007/17
በኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ቃሊቲ ኦፕሬሽን ትራኪንግ በ2017 ዓ.ም ለጋራዥ የሚያስፈልጉ የተለያዩ ቁሳቁሶች ግዥ (different types of Garage Equipment's for Heavy Trucks) ማለትም ፡-
- Lot 01. Bracket LH and Bracket RH
- Lot 02. Rubber Pad
- Lot 03. Tork Rod Bushing
- Lot 04. Different Types of Bolts with nut
- Lot 05. Different types of Consumable Goods for Heavy Duty Semi-Trailers
- Lot 06. Different size of Electrode
- Lot 07. Break Lining በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። በዚህ መሠረት:-
- ጨረታ ላይ መሳተፍ የሚፈልጉ ማንኛውም ህጋዊ ድርጅቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ያሟሉ መሆን አለበት፡፡
- ተጫራች በዘርፉ የተሰማሩበትን ህጋዊ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ ሚችሉ
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሴርተፊኬት
- የግብር ከፋይነት /Tin Number/ ምስክር ወረቀት
- በመንግሥት ንብረት ማስወገድ እና ግዥ ኤጀንሲ የተመዘገበበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች ለተወዳደሩበት ዕቃ ዋጋ ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) 2% በባንክ በተመሰከረለት ቼክ (CPO) ብቻ Ethiopian Shipping & Logistics Service Enterprise Kality Branch Office የሚል በማሠራትና ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ዘወትር በሥራ ሰዓት አስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ ቃሊቲ በሚገኘው በኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርት እና ሎጅስቲከስ ቃሊቲ ኦፕሬሽን ትራኪንግ ግዥ ዋና ክፍል ቢሮ ቁጥር 108 ቀርበው የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ጨረታ በማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ቴክኒካልና የፋይናንሺያል "posta" ኦርጂናል እና ኮፒ "posta" ላይ የጨረታ መለያ ቁጥር በመጻፍ በቅ/ጽ/ቤቱ የግዥ ዋና ክፍል ቢሮ ቁጥር 108 እስከ ጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው ህዳር 26 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 በቅ/መ/ቤቱ የስብሰባ አዳራሽ ቢሮ ቁጥር 102 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር ሁኔታዎች ጨረታ ሠነዱ ላይ የሚገኙ ሲሆን ተጨማሪ መረጃ ቢያስፈልግዎ በስልክ ቁጥር 0114-40-40-78 ወይም በአካል መጠየቅ ይችላሉ።
- ቅ/ጽ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊልም የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ ፡- የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርት እና ሎጅስቲከስ ቃሊት ኦፕሬሽን ትራኪንግ የቀድሞ ስም፡- የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ የብስ ትራንስፖርት ቃሊቲ ቅርንጫፍ በተለምዶ ቃሊቲ ጉምሩክ ግቢ ውስጥ
የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ቃሊቲ ቅ/ጽ/ቤት
