የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በሎት 1 የተሽከርካሪ ቅባቶችን፡ በሎት 2 የተሽካርካሪ ባትሪ እና በሎት-3 የተለያዩ የተሽከርካሪ መለዋወጫ ዕቃዎችን ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩና ፈቃድ ካላቸው ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥውን መፈፀም ይፈልጋል።
Ethiopian Electric Utility (የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር EEP/ST/NCB/12/2017
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በሎት 1 የተሽከርካሪ ቅባቶችን፡ በሎት 2 የተሽካርካሪ ባትሪ እና በሎት-3 የተለያዩ የተሽከርካሪ መለዋወጫ ዕቃዎችን ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩና ፈቃድ ካላቸው ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥውን መፈፀም ይፈልጋል። ስለሆነም ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ።
- ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በግዥ ኤጀንሲ የአቅራቢዎች ዝርዝር ድረ-ፅ (e-GP) ላይ የተመዘገቡ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ለመግዛት በሚመጡበት ጊዜ የጨረታ ሰነድ እንዲሸጥላቸው የጨረታ መለያ ቁጥሩን እና የግዥውን አይነት በመግለጽ፣ በሚመለከተው ኃላፊ የተፈረመ እና የድርጅቱ ማህተም ተደርጎበት ወጪ የሆነ ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- በዚህ ጨረታ ለመሳተፍ ከላይ የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች በማያያዝ መወዳደር የሚችሉ ሲሆን ዝርዝር ሁኔታው በጨረታ ሰነዱ ውስጥ ይገኛል።
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ቀንና ሰዓት ኮተቤ ብረታ ብረት ፊት ለፊት በሚገኘው ዋናው መ/ቤት ህንፃ ቁጥር-11 1ኛ ፎቅ በሚገኘው ገንዘብ ተቀባይ ቢሮ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ) በመክፈል እና የጨረታ ሰነዱን ህንፃ ቁጥር-9 1ኛ ፎቅ ግዥ ከፍል ቢሮ ቁጥር 201 በመምጣት መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቶች ከዚህ በታች ከሎት1 እስከ ሎት3 የተመለከቱትን ዕቃዎች ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ሰነዳቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታ ቁጥር EEP/ST/NCB/12/2017 የሚል ምልክት በማድረግ ከታች በተቀመጠው መሠረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
|
ተ.ቁ |
Description |
የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ |
የጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት |
የጨረታ መክፈቻ ቀንና ሰዓት |
|
ሎት-1 |
የተሽከርካሪ ቅባቶች (oil) |
90,000 (ዘጠና ሺህ ብር)
|
ህዳር 16 ቀን 2017 ዓም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት |
ህዳር 16 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት |
|
ሎት-2 |
የተሽከርካሪ ባትሪዎች (vehicle battery) |
60,000 (ስልሳ ሺህ ብር)
|
||
|
ሎት-3 |
የተሽከርካሪ መለዋወጫ ዕቃዎች (Vehicle spare parts) |
200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር)
|
- ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 011-558-06-27 መደወል ይችላሉ፡፡
- ገዥው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል
