የአዳማ ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ በ2017 የበጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ነገሮች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
Adama Hospital Medical College (የአዳማ ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ)
የጨረታ ማስታወቂያ
የአዳማ ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ በ2017 የበጀት ዓመት -
- ለጤና ባለሞያዎች ዩኒፎርም ጨርቁን በራሱ ወጪ ገዝቶ ሰፍቶ የሚያስረከብ ለአንደኛ ጊዜ ለመግዛት ማወዳደር ይፈልጋል፡፡
- ለኮሚኒቲ ፋርማሲ መድኃኒቶች ለሶስተኛ ጊዜ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- የምግብ ሸቀጣ ሸቀጦች ለህሙማን እና ለተማሪዎች የሚውል ለሶስተኛ ጊዜ ለመግዛት እና
- የተለያዩ ህትመቶች ለሶስተኛ ጊዜ ለማሳተም በግልፅ ጨረታ ማወዳደር ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩት መስፈርቶች የምታሟሉ ነጋዴዎች መወዳደር ትችላላችሁ፤
- 2016/17 ዓ.ም የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ በዘርፉ ያላችሁ
- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታከስ (VAT) ተመዝጋቢ ስለመሆኑ መረጃ ማቅረብ የሚችል
- በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ፅ/ቤት በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ መመዝገባችሁን የሚያረጋግጥ መረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዕቃ ግዥ መ/ቤት ድረስ በራሱ ወጪ ማቅረብ የሚችል፣
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የጨረታ ሰነድ ኮፒና ኦሪጅናል ለየብቻ በተለያየ ፖስታ ማሸግ አለባቸው::
- ስርዝ ድልዝ ያለው ፤ የማይታይ የጨረታ ሰነድ ወይም የዋጋ ዝርዝር ተቀባይት የለውም፡፡
- ጨረታውን ካሸነፉ በኋላ የውል ማስከበሪያ ያሸነፉበትን ዋጋ 10% ማስያዝ የሚችል፡፡
ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ኮሌጁ ግዥና ፋይናንስ የሥራ ሂደት ከፍል ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ ለኮሚኒቲ ፋርማሲ 200 /ሁለት መቶ ብር/ ለጤና ባለሞያዎች ዩኒፎርም ለምግብ ሸቀጣ ሸቀጦች እና ለተለያዩ ህትመቶች ለእያንዳንዱ 100 /መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ አለባቸው፡፡ የኮሚኒቲ ፋርማሲ መድኃኒቶች ጨረታ የሚከፈተው በ18/3/2017 ከቀኑ 8:30 እና የጤና ባለሞያዎች ዩኒፎርም በ18/03/2017 ዓ.ም 9:30 ሰዓት ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
የተለያዩ ህትመቶች ጨረታ የሚከፈተው በ19/03/2017 ከቀኑ 8፡30 እና የምግብ ሸቀጣ ሸቀጦች በ19/03/2017 ዓ.ም 9:30 ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የሚሞሉትን ዋጋ በመሥሪያ ቤቱ ሰነድ ላይ ብቻ መሆን አለበት
የጨረታ ማስከበሪያ ፡-
- ለኮሚኒቲ ፋርማሲ መድኃኒቶች 20,000 (ሃያ ሺህ) ብር
- ለጤና ባለሞያዎች ዩኒፎርም 10,000 (አስር ሺህ) ብር
- ለምግብ ሸቀጣ ሸቀጦች 6,000 (ስድስት ሺህ) ብር
- የተለያዩ ህትመቶች 10,000 (አስር ሺህ) ብር በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ "CBE, CBO, as Sineqe" ባንከ ብቻ ማስያዝ የሚችል መሆን አለበት።
መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታው በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አዳማ ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ
