Tender Detail

Tender Details

  • Deadline27 Nov 2024, 10:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Labour Outsourcing Services

የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን የተለያዩ የኤሌክትሮኒከስ መሣሪያዎችንና ለጽዳት አገልግሎት የሚውል የሰው ኃይል በኮንትራት ለመግዛት ይፈልጋል ስለሆነም የሚከተሎትን መስፈርቶች ማሟላት የምትችሉ አቅራቢዎች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡


ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን የተለያዩ የኤሌክትሮኒከስ መሣሪያዎችንና ለጽዳት አገልግሎት የሚውል የሰው ኃይል በኮንትራት ለመግዛት ይፈልጋል ስለሆነም የሚከተሎትን መስፈርቶች ማሟላት የምትችሉ አቅራቢዎች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

  1. የንግድ ምዝገባ ሰርቲፊኬት ያላቸው::
  2. አግባብነት ያለውና ከጨረታው አይነት ጋር የሚጣጣም የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው::
  3. በታክስ ባለስልጣን የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (VAT) የምዝገባ ሰርቲፊኬት ያላቸው::
  4. የግብር መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው::
  5. የዘመኑን ግብር መከፈላቸውን የሚያረጋግጥ ህጋዊ ማስረጃ አግባብነት ካለው የመንግስት መ/ቤት ማቅረብ የሚችሉ::
  6. የእቅራቢነት ምዝገባ ላይ ለመመዝገባቸው ምስከር ወረቀት ያላቸው::
  7. መ/ቤቱ ካቀረበው መስፈርት /standard / በታች ማቅረብ አይቻልም::
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለኤሌክትሮኒከስ መሳሪያዎች 1%፣ ጨረታውን ካሸነፉ ደግሞ ለውል ማስከበሪያ 10% በCPO ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ አለባቸው::
  9. የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ 200 (ሁለት መቶ) ብር ብቻ በመክፈል ከመስሪያ ቤቱ ግዥ፣ ንብረትና ፋይናንስ አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 409 ቀርበው መግዛት ይችላሉ፡፡
  10. ለመጫረት ዋጋ ያቀረቡባቸውን እቃዎች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ናሙናውን ማቅረብ አለባቸው፡፡
  11. ጨረታው የሚቆየው ለተከታታይ 15 (አስራ አምስት) የሥራ ቀናት ሲሆን ጨረታው የሚከፈተው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰአት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ4፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡ ዕለቱ የመንግስት የሥራ ቀን ካልሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
  12. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦሪጂናልና ፎቶ ኮፒውን እንዲሁም የዋጋ/Financial proposal/ እና የቴከኒኩን /Technical proposal / ለየብቻ በማሸግ በመጨረሻም አራቱንም አንድ ላይ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ የድርጅታቸውን ህጋዊ ማህተም በማድረግ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  13. ዘግይቶ የሚመጣ ፖስታ ተቀባይነት የለውም፡፡
  14. ተጫራቾች ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል መጫረት ይችላሉ፡፡
  15. ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት አ/አ/ን/ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ሳርቤት በሚገኘው የመ/ቤቱ ግምጃ ቤት ገቢ ካደረጉ በኋላ ክፍያ የሚፈጸም ይሆናል፡፡
  16. ባለስልጣን መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል መሰረዝ ይችላል፡፡

አድራሻ፡- አ/አን/ስልከ ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 4 ሳር ቤት፣ የኦሮሚያ ቢሮዎች ያሉበት ግቢ 4ኛ ፎቅ

ቢሮ ቁጥር 409 ስልከ ቁጥር፡-011-8220649

 

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የኮንስትራክሽን ባለስልጣን

Save Tender