የጌራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳው ስር ለሚገኘው መንገድ ሎጅስቲክ ጽ/ቤት ለሚያስጠግነው መንገድ ሙሉ ኮንትራት ሰጥቶ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል፤ እንዲሁም ውሃ፣ ማዕድን እና ኢነርጂ ጽ/ቤት አዲስ የውሃ ጉድጓድ ለማስቆፈር ይፈልጋል፡፡
የጌራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
የጌራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳው ስር ለሚገኘው መንገድ ሎጅስቲክ ጽ/ቤት ለሚያስጠግነው መንገድ ሙሉ ኮንትራት ሰጥቶ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል፤ እንዲሁም ውሃ፣ ማዕድን እና ኢነርጂ ጽ/ቤት አዲስ የውሃ ጉድጓድ ለማስቆፈር ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በዚህ ጨረታ ላይ ለመወዳዳር ለምትፈልጉ ተወዳዳሪዎች በሙሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው።
-
- የ2017 ዓ.ም ግብር የነበረና የንግድ ፈቃዱን ያደሰ፣
- ቲን፤ ቲኦቲ፤ ወይም የቫት ተመዝጋቢ የሆነ፣
- የጨረታ ማስከበሪያ ከአጠቃላይ ዋጋ 2% በሲፒኦ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ማስያዝ ይኖርባቸዋል
- ከመሥሪያ ቤቱ ጋር ውል ለመፈራረም ፍቃደኛ የሆነ፣
- የጨረታ ሰነዱን ለመንገድ የማይመለስ 500 (አምስት መቶ) ብር፣ ለውሃ ጉድጓድ 300 (ሶስት መቶ) ብር ለወረዳ ገቢዎች በመክፈል ግዥ ክፍል መግዛት የሚችል፤
- Withholding Tax /2%/ ለመክፈል ፍቃደኛ የሆነ፣
- በጥቃቅን እና አነስተኛ የተደራጁ ካደራጃቸው አካል ዋስትና ደብዳቤ ማረጋገጫ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ከአንድ ጊዜ በላይ ለውድድር ለቀረቡ 2% ሲፒኦ ማስያዝ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ሰነዳቸውን ዋናው እና ፎቶ ኮፒውን ለይቶ በማሸግ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ሌሎች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተንተርሰው ዋጋ ማቅረብ በህግ የተከለከለ ነው፡፡
- የመመዝገቢያ ቦታ ጌራ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 10 ይሆናል፡፡
- የመመዝገቢያ ቀን ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን 2 በኋላ ለ21 ተከታታይ ቀናቶች አየር ላይ ይቆያል፡፡ ጨረታው የሚዘጋው በ21ኛው ቀን በ6፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ቀን ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቹ ባሉበት ይከፈታል፡፡ ባይገኙም መከፈት ይችላል።
- የጨረታው አሸናፊ ለሥራው የሚያስፈልገውን ማንኛውንም ወጪ በራሱ የሚሸፈን ይሆናል።
- የሚሠራው መንገድ በኪሎ ሜትር ወይም የሚቆፈረው ጉድጓድ ብዛት በ20% ሊቀንስም ሊጨምርም ይችላል፡፡
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
*ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር: 047-342-03-03
የጌራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
