Tender Detail

Tender Details

  • Deadline10 Dec 2024, 10:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Medical Equipment And Supplies

የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ለ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት ለሆስፒታል አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች በዝርዝር የተገለፁትን በዘርፉ ከተሰማሩ ሕጋዊ የመድኃኒትና የህክምና መገልገያ አከፋፋዮችን ወይም አስመጪዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለሁለት ዓመት የሚቆይ ውል በማሰር ግዥ ማከናወን ይፈልጋል።


የጨረታ  ማስታወቂያ

የጨረታ  ቁጥር  MSF/LP/14/2024

የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ለ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት ለሆስፒታል አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች በዝርዝር የተገለፁትን በዘርፉ ከተሰማሩ ሕጋዊ የመድኃኒትና የህክምና መገልገያ አከፋፋዮችን ወይም አስመጪዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለሁለት ዓመት የሚቆይ ውል በማሰር ግዥ ማከናወን ይፈልጋል።

ጥቅል 1፡ መድሀኒቶች (MEDCINES)

ጥቅል 2፡ የላብራቶሪ ኬሚካሎችና ሪኤጀንቶች (LABORATORY CHEMICALS AND REAGENTS)

ጥቅል 3፡ የተለያዩ የህክምና መገልገያ መሳሪያዎች (MEDICAL SUPPLIES)

ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተወዳዳሪዎች እንደሚከተለው ተጋብዛችኋል

  1. በዘርፉ የተሰማራችሁ የመድኃኒትና የህከምና አከፋፋዮችን ወይም አስመጪዎችን የ2017 ዓ.ም የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላችሁ እንዲሁም የዘመኑን የመንግሥት ግብር የከፈላችሁ፤
  2. በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ መመዝገባችሁ ማቅረብ የምትችሉ፤
  3. ጉዳዩ ከሚመለከተውና አግባብነት ካለው መንግስታዊ መሥሪያ ቤት የሙያ ፈቃድ ሰርተፍኬት፤ የጥራት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ቤት ፍቀድ ማቅረብ የምትችሉ፤
  4. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ድርጅቶች ላሸነፉበት አይነት በየጊዜው በሚቀርብላቸው የግዢ ትዕዛዝ መሰረት የተለያዩ መድሃኒቶች፣ አላቂ እና ቋሚ የሕከምና መገልገያ መሣሪያዎች፣ የላብራቶሪ ኬሚካሎች እና ሪኤጀንቶች የአቅርቦት አይነት አዲስ አበባ ፊሊፕስ ህንፃ ቢሮ ቁጥር 215 ግዥ ቡድን ድረስ ማቅረብ የሚችሉ፤
  5. የጨረታ ማስከበሪያ ብር ሃምሳ ሺህ (50,000.00 ብር) በሲፒኦ /CPO/ ወይም የባንከ ዋስትና /Bid bond guarantee/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  6. መተሐራ ስኳር ፋብሪካ ግዥ ቡድን አዲስ አበባ ሜክሲኮ አደባባይ ፊሊፕስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 215 ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት የንግድ ፈቃድ ይዘው በመቅረብ ለእያንዳንዱ ጥቅል የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) እየከፈሉ የጨረታውን ሠነድ በመውሰድ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በራሳቸው የዋጋ ማቅረቢያ (Performa invoice) ላይ በማዘጋጀት በሰም በታሸገ ፖስታ በማድረግ እ.ኢት.አ. ታህሳስ 01 ቀን 2017 ዓ.ም እስከ ጠዋቱ 4:00 ሠዓት ድረስ መተሐራ ስኳር ፋብሪካ ግዥ ቡድን አዲስ አበባ ሜከሲኮ አደባባይ ፊሊፕስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 220 ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ጨረታው በዕለቱ ታህሳስ 01 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ቢሮ ቁጥር 119 ውስጥ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  9. ፋብሪካው ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

                 ስልክ ቁጥር፡- 0115 50-56-07/ 0115-50-58-21

                  አድራሻ፡- ሜክሲኮ አደባባይ ፌሲፕስ ሕንፃ

 

የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ

Save Tender