የደሴ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ እና ለደሴ ትም/መሣ/ከዘ/ስርጭት ማዕከል አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1 የጽህፈት መሣሪያ፣ ሎት 2 የጽዳት ዕቃ፣ ሎት 3 የኤሌክትሮኒከስ ዕቃ፣ ሎት 4 የህንፃ መሣሪያ፣ ሎት 5 የስፖርት ዕቃ፣ ሎት 6 የሙዚቃ መሣሪያ፣ ሎት 7 የመኪና ጎማ እና የመኪና እቃ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የደሴ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የደሴ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ እና ለደሴ ትም/መሣ/ከዘ/ስርጭት ማዕከል አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1 የጽህፈት መሣሪያ፣ ሎት 2 የጽዳት ዕቃ፣ ሎት 3 የኤሌክትሮኒከስ ዕቃ፣ ሎት 4 የህንፃ መሣሪያ፣ ሎት 5 የስፖርት ዕቃ፣ ሎት 6 የሙዚቃ መሣሪያ፣ ሎት 7 የመኪና ጎማ እና የመኪና እቃ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው::
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው::
- የግዥው መጠን ብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ የዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሠነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ከኮሌጁ ግዥ፣ ፋይ/ንብ/አስ/ ደጋፊ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 007 ማግኘት ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር— የዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጃዎች ማለትም ዋናና ቅጂ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በደሴ መም/ትም/ኮሌጅ በግዥ፣ፋይ/ንብ/አስ/ደጋፊ የሥራ ሂደት ወይም ቢሮ ቁጥር 007 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ከ 29 /02/2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 13/03/2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሠዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ፣ ፋይ/ንብ/አስ/ደጋፊ የሥራ ሂደት በቢሮ ቁጥር 007 በ13/03/2017 ዓ.ም በ8፡00 ይታሸግና በዚሁ ቀን በ8፡30 ጨረታው ይከፈታል ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ከሆነ ወደ ሚቀጥለው ቀን ይተላለፋል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 007 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0333124220 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
ማሳሰቢያ፡-
- የጽህፈት መሣሪያ፣ የጽዳት ዕቃ፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃ ፣ የህንፃ መሣሪያ ፣ የስፖርት ዕቃ ፣ የሙዚቃ መሣሪያ፣ የመኪና ጎማ በተመለከተ ጨረታው የሚወዳደረው በሎት ወይም በጥቅል ዋጋ ስለሆነ አንድም ዕቃ ቢሆን ክፍት ማድረግ ከጨረታ ውጭ ያደርጋል።
- እንዲሁም የመኪና እቃን በተመለከተ ጨረታው የሚወዳደረው በነጠላ ዋጋ ነው
- በእያንዳንዱ ጨረታ ሰነድ ላይ ሲሞሉ ስርዝ ድልዝ እንዳይኖር በጥንቃቄ ይሙሉ።
- ጨረታውን ሲሞሉ ቫትን አካተው መሙላት አለባቸው፡፡
- ሣምፕል ያቀረብናቸውን ዕቃዎች ሳምፕሉን በማየት እንድትሞሉ እናሳስባለን፡፡
የደሴ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ
