Tender Detail

Tender Details

  • Company City Administration of Addis Ababa Construction Design, Building and Consultation Enterprise (የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት)
  • Address አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ቃሊቲ ማሰልጠኛ ፊት ለፊት የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ቢሮ አጠገብ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011 4 62 14 57
  • Websitehttps://addisconstructionwork.gov.et/
  • Deadline20 Nov 2024, 10:30 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Steel, Metals And Aluminium

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮንስትራክሽን ዲዛይን፤ ግንባታና ማማከር ድርጅት ቁርጥራጭ ብረቶች ፣ ቁርጥራጭ ቆርቆሮ ና ኤጋ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

City Administration of Addis Ababa Construction Design, Building and Consultation Enterprise (የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት)


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮንስትራክሽን ዲዛይን፤ ግንባታና ማማከር ድርጅት ቁርጥራጭ ብረቶች ፣ ቁርጥራጭ ቆርቆሮ ና ኤጋ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል። ስለሆነም ከላይ የቀረቡትን ዕቃዎች ጨረታ ባሉበት ሁኔታ መሳተፍ የምትፈልጉ የማይመለስ ብር 300 ( ሶስት መቶ ብር ) በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ ቅዳሜ በአዲስ አበባ ከተማ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ቃሊቲ ማሰልጠኛ ፊት ለፊት የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ቢሮ አጠገብ የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት ቢሮ በመቅረብ የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ መግዛት ይችላሉ፡፡

  1. ተጫራቾች መግዛት የሚፈልጉትን ቁርጥራጭ አሉሚንየም፣ ቁርጥራጭ ብረቶች ፣ ቁርጥራጭ ቆርቆሮ ና ኤጋ የገዙትን የጨረታ ሰነድ በመያዝ በአካል መመልከት ይችላሉ።
  2. ተጫራቾች ለመረጧቸው ዕቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10% (አሥር ፐርሰንት) ከታወቀ ባንክ የሚሰጥ ሲፒኦ ወይም የባንከ ዋስትና /unconditional bid bond/ የመወዳደሪያ ሃሳብ ጋር በማያያዝ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል::
  3. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዋጋ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው በትክከል በመሙላት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ በተጨማሪም ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ሰነድ በታሸገ ኢንቨሎፕ በላዩ ላይ ሙሉ ስምና አድራሻ በመጻፍ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ዋጋ ተ.እ.ታ /NAT/ የማይጨምር ሲሆን የጨረታ አሸናፊዎች ለሚገዙት ዕቃ ተጨማሪ እሴት ታክስ የመክፈል ግዴታ አለባቸው ።
  5. ጨረታውን ያሸነፉ ተጫራቾች ማሸነፋቸው እንደተገለጸላቸው ያሸነፉበትን ዋጋ በቅድሚያ በመክፈል ጨረታውን ማሸነፋቸውን ከተገለጸበት ቀን አንስቶ በ10 /አሥር/ ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ ሲኖርባቸው ይህ ባይሆን ግን ድርጅቱ ጨረታውን ሰርዞ ለማስከበሪያነት የተያዘው ገንዘብ የሚወረስ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
  6. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአስራ አምስት ተከታታይ የስራ ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሆኖ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ተዘግቶ በዚሁ እለት ከጠዋቱ 5፡00 በድርጅቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ተሳታፊዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የበዓል ቀን ላይ ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡

የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡- በአዲስ አበባ ከተማ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ቃሊቲ ማሰልጠኛ ፊት ለፊት የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ቢሮ አጠገብ ስልክ ቁጥር 011 4 62 14 57

 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣

ግንባታና ማማከር ድርጅት

Save Tender

አዲስ ማሽንና መለዋወጫ ማምረቻ ኢንዱስትሪ በሀገር አቀፍና በአለም አቀፍ ደረጃ የሚገኙ በብረት ዘርፍ የተሰማሩ አምራች ድርጅቶች፣ በምርት ግብአት ወይም (Dif...

READ MORE
ድርጅታችን ለሚያከናውናቸው ልዩ ልዩ የግንባታ ስራዎች አገልግሎት የሚውሉ ግብዓቶችን እና አገልግሎቶችን በቋሚነት የሚያቀርቡ ብቁ አቅራቢዎችን (Suppliers)...

READ MORE
በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ኮንስትራክሽን ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ ለሚከናወነው የግንባታ ሥራ በዘርፉ ሕጋዊና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ተጫራቾችን በብሔራ...

READ MORE