Tender Detail

Tender Details

  • Company የአዳማ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
  • Address አዳማ በከልቻ ትራንስፖርት አክሲዮን ማህበር አጠገብ ያለው ቢሮአችን ሦስተኛ (3) ፎቅ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 022-211-58-07
  • Website
  • Deadline20 Nov 2024, 12:30 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Networking Equipment And Installation

የአዳማ ጉምሩከ ኮሚሽን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የኔትዎርክ ዝርጋታ አገልግሎት እና የዕቃ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

የአዳማ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት


በድጋሚ  የወጣ  ግልጽ  ጨረታ  ማስታወቂያ

የጨረታ  ቁጥር 05/2017

የአዳማ ጉምሩከ ኮሚሽን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የኔትዎርክ ዝርጋታ አገልግሎት እና የዕቃ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። በመሆኑም በጨረታው ለመካፈል የምትፈልጉ እና ከዚህ በታች የተዘረዘሩት መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች እንድትወዳደሩ ተጋብዛችኋል።

  1. ተጫራቾች ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /Tin/ የምስከር ወረቀት ያላቸው፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት እና በመንግስት አቅራቢነት ኤጀንሲ የተመዘገበ እንዲሁም የዘመኑን ግብር የከፈሉና ግዴታቸውን የተወጡ መሆን አለባቸው።
  2. ተጫራቾች የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣ ቀን ጀምሮ ለ15 ቀናት የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ/ በኢትዮጵያ ንግድ ባንከ አካውንት ቁጥር (በሂሳብ ቁጥራችን) 1000272296433 በአዳማ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅርጫፍ ጽ/ቤት ሥም ገቢ በማድረግ የባንክ እስሊፕ በማምጣት የጨረታ ሰነዱን በከልቻ ትራንስፖርት አክሲዮን ማህበር አጠገብ ያለው ቢሮአችን ሦስተኛ (3) ፎቅ ላይ በመቅረብ መግዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
  3. የጨረታ ሳጥኑ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ታሽጎ በዛው ቀን ከጠዋቱ 4፡35 ሰዓት በግዥና ፋይናንስ ቡድን ቢሮ ይከፈታል። ዕለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ ይከፈታል።
  4. ማንኛውም ተጫራች ለመጫረት ያቀረበው አጠቃላይ (2%) በባንከ የተመሰከረለት ሲፒኦ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ጋራንቲ በአዳማ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅርጫፍ ጽ/ቤት ስም አሰርቶ ማቅረብ አለበት። ቅ/ጽ/ቤት የተሻለ አማረጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ

የግዥና ፋይናንስ አስተዳደር ቢሮ ሶስተኛ ፎቅ

ስልክ ቁጥር 022-211-58-07/022-211-58-90

 

የአዳማ  ጉምሩክ  ኮሚሽን  ቅርንጫፍ  ጽ/ቤት

Save Tender