Tender Detail

Tender Details

  • Company በጉራጌ ዞን የምሁርና አክሊል ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
  • Address ሐዋርያት ፡ ደቡብ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0113430173
  • Website
  • Deadline24 Nov 2024, 11:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Building Construction

በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በጉራጌ ዞን የምሁርና አክሊል ወረዳ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ጽ/ቤት በ2017 መደበኛ በጀት ህጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ ከጨዛ እስከ ምድረገነት ቀበሌ ድረስ ያለው መንገድ መጠገን እና ከውቅየ እስከ የሽበትየ ድረስ የጠጠር ብተና ሥራ ማሠራት ይፈልጋል፡፡

በጉራጌ ዞን የምሁርና አክሊል ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት


ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር-0001

በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በጉራጌ ዞን የምሁርና አክሊል ወረዳ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ጽ/ቤት በ2017 መደበኛ በጀት ህጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ ከጨዛ እስከ ምድረገነት ቀበሌ ድረስ ያለው መንገድ መጠገን እና ከውቅየ እስከ የሽበትየ ድረስ የጠጠር ብተና ሥራ ማሠራት ይፈልጋል፡፡

  1. GC/RC ደረጃ 9ኝና ከዛ በላይ የግንባታ ፍቃድ ያላችሁ
  2. የንግድ ምዝገባ፣ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፤ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፤ የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣ መሆን አለባቸው፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለምሁርና አክሊል ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ/ በመክፈል ከምሁርና አክሊል ወረዳ ፋይናንስ/ፅ/ቤት ግዢ ቢሮ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21 (ሃያ አንድ) ተከታታይ ቀናት እስከ ቀኑ 5፡00 ድረስ መግዛት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታውን ቴክኒካል እና ፋይናንሽያል ዶክመንት ሲያቀርቡ፡-

ሀ. ለቴከኒካል ዶክመንት አንድ ኦርጅናልና ሁለት ቅጂ ሰነዶችን እያንዳንዳቸው በታሸገ ፖስታ በማድረግ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 30000 (ሰላሳ ሺ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ባንክ ጋራንቲ በምሁርና አክሊል ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ስም በማሠራት ከአሪጅናል ዶክመንት ጋር በማድረግ እና ሁሉንም በአንድ እናት ፖስታ ውስጥ በማሸግ ቴክኒካል በሚል በመለየት፣

ለ. ፋይናንሽያል ዶከመንት አንድ ኦርጅናልና ሁለት ቅጂ ሰነዶችን እያንዳንዳቸው በታሸገ ፖስታ በማድረግ ሁሉንም በአንድ እናት ፖስታ ውስጥ በማሸግ ፋይናንሽያል በሚል በመለየት እስከ 21ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ አላማ በተዘጋጀው የመጫረቻ ሰነድ ማቆያ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል። ከቀኑ 8፡00 ሰዓት የጨረታው ሳጥን ይታሸጋል፡፡

  1. የጨረታው ቴክኒካል ዶከመንት በሃያ አንደኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የተጫራቾች አለመገኘት ጨረታው እንዳይከፈት አያደርግም፡፡
  2. የፋይናንሽያል (የፕሮጀከቱ የግንባታ ዋጋ) ከቴክኒካል ግምገማ ውጤት በኋላ የቴክኒክ ግምገማውን ያለፉ ተጫራቾች ሰነድ ብቻ ጽ/ቤቱ በማስታወቂያ በሚገልጸው ቀን ይከፈታል፡፡
  3. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ ወደ ሚቀጥለው የሥራ ቀን ይተላለፋል።
  4. አጠቃላይ የቅሬታ አቀራረብና አፈታት በተመለከተ በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግሥት እንደገና ተሻሽሎ በወጣው ግዢ አፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 28/2010 መሰረት ይሆናል፡
  5. ጽ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

ለበለጠ መረጃ፡- 0113430173/0113430614 ይደውሉ

 

በጉራጌ ዞን የምሁርና አክሊል ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት /ሐዋርያት/

Save Tender