Tender Detail

Tender Details

  • Company የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደብረብርሀን ዲስትሪክት ጽ/ቤት
  • Address ደብረብርሀን ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0116375260
  • Website
  • Deadline06 Dec 2024, 5:00 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Land , House, Building And Warehouse

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደብረብርሀን ዲስትሪክት በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 መሰረት ቀጥሎ የተመለከተውን ንብረት ለመጀመሪያ ጊዜ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደብረብርሀን ዲስትሪክት ጽ/ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ደዲ/ጨማ/01/2017

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደብረብርሀን ዲስትሪክት በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 መሰረት ቀጥሎ የተመለከተውን ንብረት ለመጀመሪያ ጊዜ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ተ.ቁ

የተበዳሪው ስም

ያስያዡ ስም

አበዳሪው ቅርንጫፍ

የንብረት መለያ ቁጥር እና የሚገኝበት አድራሻ

የንብረቱ አገልግሎት

የጨረታ መነሻ ዋጋ

ጨረታው የሚካሄድበት

ከተማ

ቀበሌ

የቤት ካርታ ቁጥር

ቀን

ሰዓት

1

ወ/ሮ አንሻ ዘውዴ ደሴ

ወ/ሮ መዲና መሀመድ ውዶ

ጎዜ

ደብረ ብርሃን

ሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር ቀበሌ 01

አገ/4084/04

የመኖሪያ

728042.85

ህዳር 30 ቀን 2017 ዓ.ም

ከረፋዱ

4፡00-6፡00

 

ማሳሰቢያ፡-

  1. ተጫራቾች ለጨረታ ሲቀርቡ በጨረታው እለት የጨረታ መነሻ ዋጋ 1/4  ኛውን በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ ይዘው መቅረብ አለባቸው።
  2. በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ገንዘብ ወዲያውኑ ተመላሽ ይሆናል፡
  3. የጨረታው አሸናፊ ቀሪውን ገንዘብ በ15 (በአስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት ውስጥ አጠቃለው መክፈል አለባቸው። ባይከፍሉ ግን የሐራጅ ውጤቱ ተሰርዞ ያስያዙት ገንዘብ አይመለስም። ባንኩም ቤቱን እንደገና በጨረታ የመሸጥ መብቱ የተጠበቀ ነው፤
  4. የጨረታው አሸናፊ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ክፍያውን ካላጠናቀቁ ጨረታውን በፈቃዳቸው እንዳፈረሰ ተቆጥሮ ያስያዙት ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፤
  5. የጨረታው አሸናፊ የገዛውን ንብረት ስም ለማዛወር የሚከፈል ክፍያ እንዲሁም ሌሎች ተያያዥ ወጪዎችን ይሸፍናል፤
  6. ጨረታው የሚካሄደው በደብረብርሀን ዲስትሪክት ፅ/ቤት ግቢ ውስጥ ይሆናል፤
  7. ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ከዲስትሪከቱ ብድር ክፍል ጋር በመነጋገር በስራ ቀናት ወይም ባንኩ በሚያመቻቸው ፕሮግራም መሰረት ቤቱን ቦታው ድረስ ሄደው መጎብኘት ይችላሉ፤
  8. ጨረታው ባለእዳው ወይም ህጋዊ ወኪሉ፣ ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይካሄዳል፤
  9. የጨረታው አሸናፊ የሚታወቀው ባንኩ ከፍተኛ ዋጋ የሰጠው ተጫራች አሸናፊ መሆኑን ባንኩ በደብዳቤ ሲያሳውቅ ነው፤
  10. በንብረቱ ሽያጭ ላይ በመንግስት የሚጣል ግብር ታከስ የጨረታው አሸናፊ ይከፍላል።
  11. ዝርዝር መረጃ ለማግኘት ወደ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደብረብርሀን ዲስትሪክት ጽ/ቤት በአካል በመምጣት ወይም በስልከ ቁጥር 0116375260 / 0116375863 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
  12. ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደብረብርሀን ዲስትሪክት ጽ/ቤት

Save Tender