Tender Detail

Tender Details

  • Deadline19 Nov 2024, 10:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Vehicle Battery

በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የደቡብ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ ሜንቴናንስ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡


የጨረታ ማስታወቂያ

የማስታወቂያ  ቁጥር  ደ/ዕዝ ሜንቴናንስ መምሪያ ግ B-1/2017 ዓ/ም

በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የደቡብ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ ሜንቴናንስ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

  1. የተለያዩ ቀላል ቶዮታ ተሽከርካሪዎች መለዋወጫ ዕቃዎች
  2. የተለያዩ ከባድ ተሽከርካሪዎች መለዋወጫ ዕቃዎች
  3. የተለያዩ የተሸከርካሪ ጎማ
  4. አላቂ የጋራዥ መስሪያ ዕቃዎች
  5. የዳቦ ማሽን መለ/ዕቃዎችና የጀነሬተር መለ/ዕቃዎች

ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟላ ማንኛውም ህጋዊ ተጫራች በጨረታው ሊወዳደር ይችላል፡

  1. ተጫራቾች ለሚጫረቱባቸው የጨረታ ዓይነቶች ሕጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ በአቅራቢነት ስለመመዝገባቸው የአቅራቢነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፤
  2. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ /ከፋይነት/ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ።
  3. የንግድ ምዝገባ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
  4. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች ለሚጫረቱባቸው ለእያንዳንዱ ጨረታ የጨረታ ማስከበሪያ በጨረታ ሰነዱ ላይ በተገለፀው መመሪያ መሠረት በባንክ የተረጋገጠ CPO ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  6. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ የዕቃውን ዓይነት ኤንቨሎፑ ላይ በግልፅ መፃፍ ይኖርባቸዋል።
  7. የጨረታ ሰነዱን ከተጫራቾች ዝርዝር መምሪያ ጋር የማይመለስ ብር 400.00 በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ባሉት ቀናት ውስጥ ቶጋ መከላከያ ሠራዊት ካምፕ በሚገኘው የደቡብ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ ሜንቴናንስ ግዥ ቢሮ መግዛት ይቻላል።
  8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ቶጋ መከላከያ ሠራዊት ካምፕ በሚገኘው ደ/ዕዝ ጠ/መምሪያ አንደኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የመሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  9. ጨረታው ህዳር 10 ቀን 2017 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዕለቱ 4:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ደ/ዕዝ ጠ/መምሪያ አንደኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የመሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል፡፡
  10. አሸናፊ ተጫራቾች ውል ሲፈፅሙ የመልካም ስራ አፈፃፀም ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ያሸነፉበትን ዕቃ በራሳቸው ትራንስፖርት ወጭ በማጓጓዝ እና በማራገፍ ቶጋ መከላከያ ሠራዊት ካምፕ በሚገኘው የደቡብ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ ሜንቴናንስ ግምጃ ቤት ማስረከብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  11. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ እንዲሁም 20% ጨምሮ ወይም ቀንሶ የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው::

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 046 328 0019 ይደውሉ

 

የደቡብ  ዕዝ  ጠቅላይ  መምሪያ  ሜንቴናንስ ቶጋ

 

Save Tender